ኅዳር 4 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ኅዳር 4 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 43 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 14 ከአን. 1-9 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ቲቶ 1-3 እስከ ፊልሞና 1-25 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ቲቶ 2:1-15 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ የአንድ ሃይማኖታዊ ድርጅት አባል መሆን አስፈላጊ ነው?—rs ገጽ 325 አን. 2 እስከ ገጽ 326 አን. 1 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ “ለፈጠራ ወሬዎች” ትኩረት ከመስጠት መቆጠብ ያለብን ለምንድን ነው?—1 ጢሞ. 1:3, 4፤ 2 ጢሞ. 4:3, 4 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ በኅዳር ወር መጽሔቶችን ለማበርከት የሚረዱ ሐሳቦች። በውይይት የሚቀርብ፤ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አድማጮችን ጠይቅ፦ የመንግሥት ዜና ቁጥር 38ን በምናበረክትበት ወቅት ሁኔታው አመቺ ከሆነ ቅዳሜና እሁድ መጽሔቶችን ማበርከት ያለብን ለምንድን ነው? ይህን ለማድረግ የሚያስችሉን አጋጣሚዎች የትኞቹ ናቸው? ውይይታችንን ከመንግሥቱ ዜናው ወደ መጽሔቶቹ ለማዞር ምን ማለት እንችላለን? እያንዳንዱን መጽሔት ከመንግሥቱ ዜና ቁጥር 38 ጋር እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ የአምላክ ቃል ኃይለኛ ነው። (ዕብ. 4:12) በ2013 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ከገጽ 57 አንቀጽ 1 እስከ ገጽ 59 አንቀጽ 3 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። ምን ትምህርት እንዳገኙ አድማጮችን ጠይቅ።
መዝሙር 37 እና ጸሎት