ጥር 20 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ጥር 20 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 34 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 17 ከአን. 16-20 እና ሣጥን (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 11-16 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 14:17 እስከ 15:11 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ፦ ‘ትክክለኛ የሆነ አንድ ሃይማኖት ብቻ አለ ለማለት የሚያበቃችሁ ምንድን ነው?’—rs ገጽ 331 አን. 4 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አብዶን—የጥልቁ መልአክ—ማን ነው?—re ገጽ 143, 148 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ምን ትምህርት እናገኛለን? በውይይት የሚቀርብ። ማቴዎስ 7:6-11 እንዲነበብ አድርግ። ከዚያም ይህ ዘገባ ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ ሊጠቅመን የሚችለው እንዴት እንደሆነ ተወያዩበት።
10 ደቂቃ፦ በመካከላችሁ በትጋት እየሠሩ ያሉትን አክብሯቸው። (1 ተሰ. 5:12, 13) በውይይት የሚቀርብ፤ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አድማጮችን ጠይቅ፦ (1) ሽማግሌዎች በጉባኤ ውስጥ በትጋት እየሠሩ ያሉት በየትኞቹ መንገዶች ነው? (2) ለሽማግሌዎች የላቀ አክብሮት ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? (3) ግንባር ቀደም ሆነው የሚመሩን ወንድሞች ማበረታቻ የሚያስፈልጋቸው ለምንድን ነው? (4) ሽማግሌዎችንም ሆነ ቤተሰባቸውን ማበረታታት የምንችለው እንዴት ነው? (5) ግንባር ቀደም ሆነው ለሚመሩን ወንድሞች መታዘዝ ለጉባኤውም ሆነ ለሽማግሌዎች የሚጠቅመው እንዴት ነው?
10 ደቂቃ፦ “የአገልግሎት ጓደኛችሁን አበረታቱ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። በአገልግሎት ላይ ከሌሎች ጋር ሲያገለግሉ የተማሩትን ጠቃሚ ነገር እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
መዝሙር 45 እና ጸሎት