ጥር 27 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ጥር 27 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 27 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 18 ከአን. 1-9 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 17-20 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 17:18 እስከ 18:8 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ኢየሱስ ወደ ሰማይ የሄደው ሥጋዊ አካል ይዞ አይደለም—rs ገጽ 333 አን. 2-4 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አባ—“አባ” የሚለው ቃል በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ የተሠራበት እንዴት ነው? ሰዎች ተገቢ ባልሆነ መንገድ የተጠቀሙበትስ እንዴት ነው?—w00 11/15 ገጽ 19፤ w09 4/1 ገጽ 13 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ በመጀመሪያው ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር። በንግግር የሚቀርብ። ከዚያም በጥቅምት ወር የመጀመሪያ ቅዳሜ ጉባኤው ለመስክ አገልግሎት ያደረገውን ዝግጅት ጥቀስ፤ እንዲሁም ሁሉም ጥናት ለማስጀመር ጥረት እንዲያደርጉ አበረታታ። በቅርብ ጊዜ ለደረሰን መጠበቂያ ግንብ የተዘጋጀውን የአቀራረብ ናሙና በመጠቀም አንድ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
15 ደቂቃ፦ መንፈሳዊ ግቦችህ ምንድን ናቸው? የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ገጽ 117 ከአንቀጽ 1 እስከ ምዕራፉ መጨረሻ ድረስ ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ግብ ላይ ለደረሱ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግ። ከሌሎች ምን ማበረታቻ አግኝተዋል? የትኞቹን መሰናክሎች አልፈዋል? ምን በረከትስ አግኝተዋል?
10 ደቂቃ፦ “የመጽሔት ደንበኞች ማፍራት ጥናት ለማስጀመር ጥሩ በር ይከፍታል።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። የመጽሔት ደንበኛቸው የነበረን ሰው ከጊዜ በኋላ ጥናት ማስጀመር የቻሉት እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
መዝሙር 45 እና ጸሎት