የካቲት 17 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
የካቲት 17 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 15 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 29-31 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 29:21-35 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ትንሣኤ ለሰው ልጆች በአጠቃላይ ምን ትርጉም አለው?—rs ገጽ 336 አን. 1-4 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ታማኝነት—ምን ጥቅም አለው?—w05 9/1 ገጽ 4-7 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ በምትሰብኩበት ጊዜ ወዳጃዊ ስሜት ይኑራችሁ። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 118 አንቀጽ 1 እስከ ገጽ 119 አንቀጽ 5 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ።
5 ደቂቃ፦ በአገልግሎት ላይ jw.org የተባለውን ድረ ገጽ እየተጠቀማችሁበት ነው? በውይይት የሚቀርብ። አድማጮች jw.org የተባለውን ድረ ገጽ በአገልግሎት ላይ በመጠቀም ያገኟቸውን ግሩም ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ። አድማጮች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ jw.orgን እንዲያስተዋውቁ አበረታታ።
15 ደቂቃ፦ “የመታሰቢያው በዓል የሚከበርበት ወቅት አስደሳች እንዲሆንላችሁ አድርጉ!” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። የጤና ችግር ቢኖርባቸውም ወይም ፕሮግራማቸው የተጣበበ ቢሆንም ረዳት አቅኚ ለመሆን እቅድ ያወጡ የጉባኤው አባላት ስላደረጉት ማስተካከያ እንዲናገሩ ጋብዝ። አንቀጽ 3 ላይ ስትወያዩ ጉባኤው በመጋቢት፣ በሚያዝያ እና በግንቦት ወራት ለመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ ምን ዝግጅት እንዳደረገ እንዲናገር የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹን ጋብዝ።
መዝሙር 8 እና ጸሎት