መጋቢት 17 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መጋቢት 17 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 37 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
jl ትምህርት 11-13 (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 43-46 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 44:18-34 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ምድራዊ ትንሣኤ የሚያገኙት እነማን ናቸው?—rs ገጽ 338 አን. 4 እስከ ገጽ 339 አን. 4 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አቢያ—ይሖዋ በሰዎች ልብ ውስጥ ያለውን መልካም ነገር ያያል—w10 7/1 ገጽ 29 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
15 ደቂቃ፦ በምንሰብክበት ወቅት በአነጋገራችን ዘዴኛ መሆን። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 197 አንቀጽ 1 እስከ ገጽ 199 አንቀጽ 4 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። አንድ አስፋፊ በአካባቢያችሁ ለሚያጋጥም አንድ የተቃውሞ ሐሳብ ዘዴ በጎደለው መንገድ ምላሽ ሲሰጥ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ከዚያም አስፋፊው ለዚያው የተቃውሞ ሐሳብ ዘዴ በተሞላበት መንገድ መልስ ሲሰጥ የሚያሳይ ሌላ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
15 ደቂቃ፦ “አጋጣሚውን ትጠቀሙበታላችሁ?” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚደረገውን ልዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ በምን መንገድ ለማንበብ ዝግጅት እንዳደረጉ ሐሳብ እንዲሰጡ አድማጮችን ጋብዝ። የመታሰቢያውን በዓል አስመልክቶ ጉባኤው ያደረጋቸውን ዝግጅቶች ተናገር።
መዝሙር 8 እና ጸሎት