ሚያዝያ 7 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሚያዝያ 7 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 15 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
jl ትምህርት 20-22 (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፀአት 7-10 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘፀአት 9:20-35 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ኢየሱስ የሚመለሰው እንዴት ነው? ዓይኖች ሁሉ የሚያዩትስ እንዴት ነው?—rs ገጽ 341 አን. 5 እስከ ገጽ 343 አን. 2 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አቢሳ—ታማኝ ሁኑ፤ ወንድሞቻችሁን ለመርዳትም ዝግጁ ሁኑ—w13 1/15 ገጽ 30-31 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ በሚያዝያ ወር መጽሔቶችን አበርክቱ። በውይይት የሚቀርብ። በቅድሚያ በዚህ ገጽ ላይ የሚገኙትን ሁለት የአቀራረብ ናሙናዎች በመጠቀም መጽሔቶቹን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ከዚያም እያንዳንዱን የአቀራረብ ናሙና ከመክፈቻው ሐሳብ ጀምሮ እስከ መደምደሚያው ድረስ ተራ በተራ ተወያዩበት። ሁሉም ከመጽሔቶቻችን ጋር በደንብ እንዲተዋወቁና በቅንዓት እንዲያሰራጩ አጠር ያለ ማበረታቻ በመስጠት ክፍልህን ደምድም።
10 ደቂቃ፦ እንግዳ ተቀባይ መሆንን አትርሱ። (ዕብ. 13:1, 2) በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ጉባኤው ለመታሰቢያው በዓል ያደረጋቸውን ዝግጅቶች ተናገር። በበዓሉ ላይ ለሚገኙ እንግዶችም ሆነ ለቀዘቀዙ አስፋፊዎች የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ ማሳየት የምንችልባቸውን አንዳንድ መንገዶች ጥቀስ። ሁለት ክፍሎች ያሉት አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። የመጀመሪያው ክፍል አንድ አስፋፊ መጋበዣ ወረቀት ደርሶት ለመጣ ሰው ከፕሮግራሙ በፊት ጥሩ አቀባበል ሲያደርግለት የሚያሳይ ነው። ሁለተኛው ደግሞ አስፋፊው፣ ከፕሮግራሙ በኋላ ፍላጎት ያሳየውን ግለሰብ ተከታትሎ ለመርዳት ለሌላ ጊዜ ቀጠሮ ሲይዝ የሚያሳይ ነው።
10 ደቂቃ፦ ምን ውጤት አገኘን? በውይይት የሚቀርብ። አስፋፊዎች “በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ውይይት የሚያስቆሙ ሐሳቦች ሲሰነዘሩ መልስ መስጠት” በሚለው ርዕስ ላይ የቀረቡትን ነጥቦች ተግባራዊ በማድረጋቸው ምን ጥቅም እንዳገኙ ሐሳብ እንዲሰጡ ጠይቃቸው፤ እንዲሁም ያገኙትን ግሩም ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 20 እና ጸሎት