ነሐሴ 4 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ነሐሴ 4 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 51 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 5 ከአን. 9-16 እና በገጽ 41, 42 ላይ የሚገኙ ሣጥኖች (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 4-6 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘኍልቍ 4:17-33 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ መጽሐፍ ቅዱስ አንዳንዶች ፈጽመው እንደማይድኑ ይናገራል?—rs ገጽ 357 አን. 1-3 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ክስ—ይሖዋ የሐሰት ክስ በሚሰነዝሩ ሰዎች ላይ ይፈርዳል—w08 11/15 ገጽ 18-19፤ w10 7/15 ገጽ 12-15 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ በነሐሴ ወር መጽሔቶችን አበርክቱ። በውይይት የሚቀርብ። ቅዳሜና እሁድ በልዩ ዘመቻው ስትካፈሉ በዚህ ገጽ ላይ የሚገኙትን የአቀራረብ ናሙናዎች በመጠቀም መጽሔቶቹን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ከዚያም አድማጮች በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ፦ በነሐሴ ወር ቅዳሜና እሁድ ስናገለግል ሁኔታው አመቺ ከሆነ መጽሔቶችን ለማበርከት ጥረት ማድረግ የሚኖርብን ለምንድን ነው? መጽሔት ማበርከት የምንችልባቸው አንዳንድ አጋጣሚዎች የትኞቹ ናቸው?
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት ወይም “ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግ የሚያስገኘው ደስታ።” (1 ቆሮ. 3:8) ተመላልሶ መጠየቅ በማድረግ ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በማስጀመር ረገድ ያገኙትን ተሞክሮ እንዲናገሩ ለሁለት አስፋፊዎች ቃለ መጠይቅ አድርግ። “እንዲህ እንድታደርጉ ያነሳሳችሁ ምንድን ነው?” “ውጤታማ እንድትሆኑ የረዳችሁ ምንድን ነው?” በማለት ጠይቃቸው። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ተመልሰው እንዲጠይቁ ሁሉንም አበረታታ።
10 ደቂቃ፦ ምን ውጤት አገኘን? በውይይት የሚቀርብ። አስፋፊዎች “በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ከሰዎች ጋር ውይይት በመጀመር መደበኛ ባልሆነ መንገድ መመሥከር” በሚለው ርዕስ ላይ የቀረቡትን ነጥቦች ተግባራዊ በማድረጋቸው ምን ጥቅም እንዳገኙ ሐሳብ እንዲሰጡ ጠይቃቸው። እንዲሁም ያገኙትን ግሩም ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 28 እና ጸሎት