ነሐሴ 11 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ነሐሴ 11 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 38 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 5 ከአን. 17-22 (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 7-9 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘኍልቍ 9:9-23 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ አንዴ የዳነ ለሁልጊዜ ድኗል ማለት አይደለም—rs ገጽ 357 አን. 4-7 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አካን—ከአምላክ መስረቅ አስከፊ ውጤት ያስከትላል—w10 4/15 ገጽ 20-21፤ w04 12/1 ገጽ 11 አን. 4 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ “1914-2014—የአምላክ መንግሥት የመቶ ዓመት የግዛት ዘመን!” በውይይት የሚቀርብ። በዚህ ገጽ አናት ላይ የሚገኘው አንቀጽ እንዲነበብ አድርግ። በዚህ ወር በአገልግሎት ስብሰባ ላይ የሚቀርቡት ክፍሎች በመንግሥቱ ላይ ያተኮሩ ናቸው። ጉባኤው ለመስክ አገልግሎት ያደረገውን ዝግጅት ግለጽ።
10 ደቂቃ፦ “የድረ ገጹን ትራክት ተጠቀሙ።” ትራክቱ በያዘው ሐሳብ ላይ ተወያዩ። አንድ አስፋፊ ትራክቱን ሲያበረክት፣ ከዚያም በኤሌክትሮኒክ መሣሪያ ተጠቅሞ ግለሰቡን ወደ jw.org ሲመራው የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
15 ደቂቃ፦ “በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ስለ መንግሥቱ በድፍረት መናገር።” በውይይት የሚቀርብ። ሁለት አስፋፊዎች የሚከተለውን ሁኔታ በሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርቡ አድርግ፦ አንድ አስፋፊ ወረፋ እየጠበቀ ነው። አብሮት የተሰለፈ አንድ ሰው አንድ ጋዜጣ ተመልክቶ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ዓለም ከቁጥጥር ውጪ እየሆነ ሄዷል። ሁሉም ሰው መፍትሔ አለኝ ይላል፤ ችግሮቹ ግን ከቀን ወደ ቀን እየተባባሱ ነው።” አስፋፊው በመነባንብ መልክ የሚከተለውን ይናገራል፦ ‘አንድ ነገር ማለት አለብኝ። ስለ መንግሥቱ መናገር ይኖርብኛል!’ ከዚያም አስፋፊው እንዲህ ይላል፦ “ልክ ነህ፤ የምንሰማው ሁሉ መጥፎ ዜና ብቻ ሆነ አይደል? ይህን ትራክት ልስጥህ? በትራክቱ ላይ የተገለጸው ድረ ገጽ በሰዎች አእምሮ ለሚጉላሉ በርካታ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት እንድችል ረድቶኛል።” አስፋፊው ከትራክቱ ላይ አንድ ነጥብ ይጠቅሳል፤ ከዚያም ግለሰቡ ፍላጎት እንዳለው ያሳያል።
መዝሙር 47 እና ጸሎት