ነሐሴ 25 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ነሐሴ 25 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 2 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 6 ከአን. 9-16 (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 14-16 (10 ደቂቃ)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ (20 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ከጉባኤው የተገኙ ተሞክሮዎች። አስፋፊዎች ስለ መንግሥቱ በድፍረት ሲናገሩ የሚያሳዩ በጉባኤያችሁ ክልል ውስጥ የተገኙ አንድ ወይም ሁለት ተሞክሮዎች በሠርቶ ማሳያ መልክ እንዲቀርቡ አድርግ። በዕብራውያን 6:11, 12 ላይ በአጭሩ በመወያየት መንግሥቱን ለማስታወቅ በትጋት መሥራታችን አስፈላጊ መሆኑን ጎላ አድርገህ ጥቀስ።
10 ደቂቃ፦ ስለ አምላክ መንግሥት ማብራራት—ክፍል 1 በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 280 ከአንቀጽ 1-4 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
15 ደቂቃ፦ ስለ አምላክ መንግሥት ማብራራት—ክፍል 2 በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 280 አንቀጽ 5 እስከ ገጽ 281 አንቀጽ 1 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። አንድ አስፋፊ የአምላክ መንግሥት እውን መስተዳድር እንደሆነ ለአንድ ሰው ሲያስረዳ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 10 እና ጸሎት