የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ነሐሴ 25, 2014 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው።
ዘሌዋውያን 18:3 ትክክል እና ስህተት ስለሆነው ነገር ያለን አመለካከት የተዛባ እንዳይሆን የሚረዳን እንዴት ነው? (ኤፌ. 4:17-19) [ሐምሌ 7, w02 2/1 ገጽ 29 አን. 4]
በዘሌዋውያን 19:2 ላይ የሚገኘው ትእዛዝ ምን ያስተምረናል? ይህን ትእዛዝ ለማክበር ጥረት ማድረግ ያለብንስ ለምንድን ነው? [ሐምሌ 7, w09 7/1 ገጽ 9 አን. 5]
ቃርሚያን በተመለከተ በጥንት ጊዜ ከተሰጠው ሕግ በስተጀርባ ያለው መሠረታዊ ሥርዓት ምን ያስተምረናል? (ዘሌ. 19:9, 10) [ሐምሌ 7, w06 6/15 ገጽ 22-23 አን. 13]
“በዐይን ፈንታ ዐይን” የሚለው ትእዛዝ በቀልን የሚያበረታታ አይደለም የምንለው ለምንድን ነው? (ዘሌ. 24:19, 20) [ሐምሌ 14, w09 9/1 ገጽ 22 አን. 3-4]
አንድ እስራኤላዊ ወለድ ማስከፈል የማይፈቀድለት በምን ዓይነት ሁኔታዎች ውስጥ ነው? ወለድ ማስከፈል የሚፈቀድለትስ መቼ ነው? (ዘሌ. 25:35-37) [ሐምሌ 21, w04 5/15 ገጽ 24 አን. 3]
የእስራኤል ነገዶች 13 ሆነው ሳለ መጽሐፍ ቅዱስ አብዛኛውን ጊዜ 12 እንደሆኑ አድርጎ የሚናገረው ለምንድን ነው? (ዘኍ. 1:49, 50) [ሐምሌ 28, w08 7/1 ገጽ 21]
በዘኍልቍ 8:25, 26 ላይ ከሚገኘው ሌዋውያን በቤተ መቅደሱ ስለሚያከናውኑት አገልግሎት ከሚገልጸው ዘገባ በዕድሜ ለገፉ ሰዎች አሳቢነት ማሳየትን በተመለከተ ምን ትምህርት እናገኛለን? [ነሐሴ 11, w04 8/1 ገጽ 25 አን. 1]
እስራኤላውያን ከግብፅ ሲወጡ ብዙ ተአምራትን ቢመለከቱም አጉረምራሚዎች የሆኑት ለምንድን ነው? ከዚህ ዘገባ ምን ትምህርት እናገኛለን? (ዘኍ. 11:4-6) [ነሐሴ 18, w95 3/1 ገጽ 16 አን. 10]
ኤልዳድና ሞዳድ ትንቢት መናገር በጀመሩበት ወቅት ሙሴ ምላሽ ከሰጠበት መንገድ ምን እንማራለን? (ዘኍ. 11:27-29) [ነሐሴ 18, w04 8/1 ገጽ 26 አን. 5]
እስራኤላውያን ‘በልብሳቸው ጫፍ ላይ ዘርፍ እንዲያደርጉ’ ከተሰጠው ትእዛዝ ምን ጠቃሚ ትምህርት እናገኛለን? (ዘኍ. 15:37-39) [ነሐሴ 25, w04 8/1 ገጽ 26 አን. 8]