መስከረም 29 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መስከረም 29 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 11 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 8 ከአን. 1-7 እና በገጽ 61 እና 62 ላይ የሚገኙ ሣጥኖች (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 33-36 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘኍልቍ 33:24-49 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ የዲያብሎስን ኃይል አቅልላችሁ አትመልከቱት—rs ገጽ 363 አን. 2 እስከ ገጽ 364 አን. 1 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አስተዳደር—አምላክ ከ33 ዓ.ም. ጀምሮ ያቋቋመው “አስተዳደር”—w06 2/15 ገጽ 17-19፤ w12 7/15 ገጽ 27-28 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ በመጀመሪያው ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር። በውይይት የሚቀርብ። በገጽ 4 ላይ የሚገኘውን የአቀራረብ ናሙና በመጠቀም በጥቅምት ወር የመጀመሪያ ቅዳሜ እንዴት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። እንዲሁም ሁሉም ጥናት ለማስጀመር ጥረት እንዲያደርጉ አበረታታ።
10 ደቂቃ፦ ምን ትምህርት እናገኛለን? በውይይት የሚቀርብ። የሐዋርያት ሥራ 4:13 እና 2 ቆሮንቶስ 4:1, 7 እንዲነበቡ አድርግ። ከዚያም እነዚህ ጥቅሶች ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ ሊጠቅሙን የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ተወያዩበት።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው የሽማግሌዎች አካል አስተባባሪ ቃለ መጠይቅ ማድረግ። በጉባኤው ውስጥ ምን ኃላፊነቶችን ትወጣለህ? በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ክፍሎችን ስትደለድል ግምት ውስጥ የምታስገባቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? የሽማግሌዎች አካል አስተባባሪ፣ የሽማግሌዎች አካል ወይም የጉባኤው ኃላፊ እንደሆነ ተደርጎ መቆጠር የማይገባው ለምንድን ነው?
መዝሙር 4 እና ጸሎት