የካቲት 23 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
የካቲት 23 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 21 እና ጸሎት
bt ምዕ. 15 ከአን. 8-12 እና በገጽ 118 ላይ የሚገኝ ሣጥን (30 ደቂቃ)
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መሳፍንት 19-21 (8 ደቂቃ)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ (20 ደቂቃ)
የወሩ ጭብጥ፦ ‘ለመልካም ሥራ የምትቀኑ’ ሁኑ!—ቲቶ 2:14
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ እንደ ኢየሱስ ለእውነተኛው አምልኮ ቅንዓት ይኑራችሁ። በግንቦት 15, 2013 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 8 አንቀጽ 2 እና በታኅሣሥ 15, 2010 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 9-11 ከአንቀጽ 12-16 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። የስብከቱ ሥራ ክርስቲያኖች ሊሠሩት የሚገባ “መልካም ሥራ” የሆነው እንዴት እንደሆነ ጥቀስ። (ቲቶ 2:14) እውነትን ማወቃችን ምሥራቹን በቅንዓት እንድንሰብክና ሰዎችን መጽሐፍ ቅዱስ እንድናስጠና የሚገፋፋን እንዴት እንደሆነ ተናገር። ጉባኤው ለመልካም ሥራ ያሳየውን ቅንዓት ጠቅሰህ አመስግን።
10 ደቂቃ፦ “ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን እውነት በቅንዓት አውጁ።” በውይይት የሚቀርብ። አንድ አስፋፊ በግንቦት 15, 2014 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 8 አንቀጽ 8 ላይ በሚገኘው “ምሳሌ 1” ላይ ተመሥርቶ ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ አድርግ፤ እንዲሁም በገጽ 9 አንቀጽ 13 ላይ ያለውን ምሳሌ ይጠቀማል።
መዝሙር 5 እና ጸሎት