ግንቦት 25 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ግንቦት 25 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 56 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 19 ከአን. 1-5 እና በገጽ 149 እና 150 ላይ የሚገኙት ሣጥኖች (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ሳሙኤል 13-15 (8 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ 2 ሳሙኤል 13:34 እስከ 14:7 (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ መጽሐፍ ቅዱስ ሥራን አስመልክቶ ምን ይላል?—nwt ገጽ 24 አን. 1-3 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ባስልኤል—ጭብጥ፦ የይሖዋ መንፈስ የአምላክ አገልጋዮች ለማንኛውም መልካም ሥራ ብቁ እንዲሆኑ ያስታጥቃል—w11 12/15 ገጽ 18 አን. 6-8 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
የወሩ ጭብጥ፦ ሁሉም ዓይነት ሰዎች የእውነትን ትክክለኛ እውቀት እንዲያገኙ እርዷቸው።—1 ጢሞ. 2:3, 4
10 ደቂቃ፦ ለመስክ አገልግሎት ቡድን የበላይ ተመልካች ቃለ መጠይቅ ማድረግ። የተሰጠህ ኃላፊነት ምን ነገሮችን ያካትታል? በቡድንህ ውስጥ ላሉት አስፋፊዎች እረኝነት የምታደርገው እንዲ ሁም በአገልግሎታቸው የምትረዳቸው እንዴት ነው? አስፋፊዎች መኖሪያቸውን ወይም አድራሻቸውን ሲቀይሩ ለአንተ ማሳወቃቸው አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ሁሉም የመስክ አገልግሎት ቡድኖች አንድ ላይ የስምሪት ስብሰባ እንዲያካሂዱ ከማድረግ ይልቅ ሽማግሌዎች እያንዳንዱ የመስክ አገልግሎት ቡድን ለየብቻው የስምሪት ስብሰባ እንዲያካሂድ ሊያደርጉ የሚችሉት ለምንድን ነው?
20 ደቂቃ፦ “ዓይነ ስውራን ስለ ይሖዋ እንዲማሩ እርዷቸው።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 96 እና ጸሎት