የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ነሐሴ 31, 2015 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው።
ሰለሞን ባቀረበው ጸሎት ላይ ስለ ይሖዋ አምላክ ምን እምነት የሚያጠናክሩ እውነቶችን ጠቅሷል? በእነዚህ እውነቶች ላይ ማሰላሰላችን የሚጠቅመን እንዴት ነው? (1 ነገ. 8:22-24, 28) [ሐምሌ 6, w05 7/1 ገጽ 30 አን. 3]
ዳዊት “በንጹሕ ልብ” በመሄድ የተወው ምሳሌ እኛም ተመሳሳይ ነገር እንድናደርግ የሚያበረታታን እንዴት ነው? (1 ነገ. 9:4) [ሐምሌ 13, w12 11/15 ገጽ 7 አን. 18-19]
ይሖዋ ኤልያስን በሰራፕታ ወደምትኖረው መበለት እንደላከው የሚገልጸው ዘገባ ምን ጠቃሚ ትምህርት ይዟል? (1 ነገ. 17:8-14) [ሐምሌ 27, w14 2/15 ገጽ 14]
በአንደኛ ነገሥት 17:10-16 ላይ በሚገኘው ዘገባ ላይ ማሰላሰላችን ምንጊዜም በይሖዋ ለመታመን ያደረግነውን ቁርጥ ውሳኔ የሚያጠናክርልን እንዴት ነው? [ሐምሌ 27, w14 2/15 ገጽ 13-15]
የተስፋ መቁረጥ ስሜትን በመቋቋም ረገድ ከኤልያስ ምን እንማራለን? (1 ነገ. 19:4) [ነሐሴ 3, ia ገጽ 102-103 አን. 10-12፤ w14 3/15 ገጽ 15 አን. 15-16]
ይሖዋ የእሱ ታማኝ አገልጋይ የሆነው ነቢዩ ኤልያስ በተስፋ መቁረጥ ስሜት ተውጦ ሲመለከት ምን ተሰማው? እኛስ አፍቃሪ የሆነውን አምላካችንን መምሰል የምንችለው እንዴት ነው? (1 ነገ. 19:7, 8) [ነሐሴ 3, w14 6/15 ገጽ 27 አን. 15-16]
ንጉሥ አክዓብ ምን ዓይነት የተሳሳተ አመለካከት ነበረው? በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖችስ ተመሳሳይ ስህተት ከመሥራት መቆጠብ የሚችሉት እንዴት ነው? [ነሐሴ 10, lv ገጽ 164-165፣ ሣጥን፤ w14 2/1 ገጽ 14 አን. 3-4]
ኤልሳዕ ለኤልያስ ካቀረበው ጥያቄ ምን ትምህርት እናገኛለን? ይህ ዘገባ በተለይ አዲስ የአገልግሎት ምድብ በምንቀበልበት ወቅት ሊረዳን የሚችለው እንዴት ነው? (2 ነገ. 2:9, 10) [ነሐሴ 17, w03 11/1 ገጽ 31 አን. 5-6]
ታዳጊ ወጣቶች፣ በሁለተኛ ነገሥት 5:1-3 ላይ የተጠቀሰችውን እምነትና ድፍረት ያሳየችውን እስራኤላዊት ልጅ ምሳሌ መከተል የሚችሉት እንዴት ነው? [ነሐሴ 24, w12 2/15 ገጽ 12-13 አን. 11]
ባለንበት በመጨረሻው ዘመን ያሉ የይሖዋ አገልጋዮች በሙሉ ኢዩ ያሳያቸውን የትኞቹን ባሕርያት ማዳበር አለባቸው? (2 ነገ. 10:16) [ነሐሴ 31, w11 11/15 ገጽ 5 አን. 5]