ነሐሴ 31 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ነሐሴ 31 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 42 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 23 ከአን. 16-19 እና በገጽ 188 ላይ የሚገኝ ሣጥን (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 9-11 (8 ደቂቃ)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ (20 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
የወሩ ጭብጥ፦ “እኔና ቤተሰቤ ግን ይሖዋን እናገለግላለን።” —ኢያሱ 24:15
10 ደቂቃ፦ በመስከረም ወር መጽሔቶችን አበርክቱ። በውይይት የሚቀርብ። በቅድሚያ የአቀራረብ ናሙናዎቹን በመጠቀም ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ከዚያም በእያንዳንዱ የአቀራረብ ናሙና ላይ ተወያዩበት።
10 ደቂቃ፦ ‘በተገቢው ጊዜ ምግብ’ እያገኘህ ነው? በነሐሴ 15, 2014 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 3-5 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። ሁሉም የሚቀርብላቸውን መንፈሳዊ ምግብ በደንብ እንዲመገቡ አበረታታ።
10 ደቂቃ፦ ለ2016 የአገልግሎት ዓመት ምን ዓይነት መንፈሳዊ ግቦች አውጥተሃል? የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ገጽ 118 አንቀጽ 3 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። አንድ ባልና ሚስት ለአዲሱ የአገልግሎት ዓመት ያወጧቸውን መንፈሳዊ ግቦች በተመለከተ ሲወያዩ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 10 እና ጸሎት