መስከረም 7 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መስከረም 7 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 3 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 24 ከአን. 1-9 እና በገጽ 193 ላይ የሚገኝ ሣጥን (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 12-15 (8 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ 2 ነገሥት 13:12-19 (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ዶርቃ—ጭብጥ፦ እውነተኛ ክርስቲያኖች መልካም ነገሮችን በማድረግ ይተጋሉ—bt ገጽ 66 አን. 23-24፤ w11 8/1 ገጽ 14-15 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ በክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙት መጻሕፍት ምን ይዘዋል?—nwt ገጽ 35 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
የወሩ ጭብጥ፦ “እኔና ቤተሰቤ ግን ይሖዋን እናገለግላለን።” —ኢያሱ 24:15
10 ደቂቃ፦ ምን ውጤት አገኘን? በውይይት የሚቀርብ። አስፋፊዎች “በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—አዲሶችን ማሠልጠን” በሚለው ርዕስ ላይ የቀረቡትን ነጥቦች ተግባራዊ በማድረጋቸው ምን ጥቅም እንዳገኙ ሐሳብ እንዲሰጡ ጠይቃቸው። እንዲሁም ያገኙትን የሚያበረታታ ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ።
10 ደቂቃ፦ ቤተሰቦች፣ በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ አዘውትሮ የመገኘት ልማድ አላችሁ? በዕብራውያን 10:24, 25 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። ልጆች ላሉት አንድ ቤተሰብ ቃለ ምልልስ አድርግ። የቤተሰቡ ራስ ለስብሰባዎች ቅድሚያ እንደሚሰጥ የሚያሳየው እንዴት ነው? ሁሉም በስብሰባዎች ላይ አዘውትረው እንዲገኙ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ምን አስተዋጽኦ ማበርከት ይችላል? በስብሰባዎች ላይ የሚሰጡትን ሐሳብ የሚዘጋጁት መቼ ነው? ከስብሰባ ላለመቅረት ምን መሥዋዕት ይከፍላሉ? ሁሉም በስብሰባዎች ላይ አዘውትረው እንዲገኙና ተሳትፎ እንዲያደርጉ በማበረታታት ክፍሉን ደምድም።
10 ደቂቃ፦ የመጽሐፍ ቅዱስን የእውነት ዘር በዘመዶችህ ልብ ውስጥ መዝራት ትችላለህ? (ሥራ 10:24, 33, 48) በ2015 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ገጽ 87 አንቀጽ 1-2 እና ገጽ 90 ከአንቀጽ 1-3 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። አድማጮች ምን ትምህርት እንዳገኙ ጠይቅ።
መዝሙር 118 እና ጸሎት