ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ነሐሴ፦ ከአምላክ የተላከ ምሥራች! መስከረም እና ጥቅምት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ኅዳር፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ወይም የሚከተሉት ትራክቶች፦ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን አመለካከት አለህ? (T-30)፣ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ምን ይሰማሃል? (T-31)፣ የቤተሰብን ሕይወት አስደሳች ለማድረግ ቁልፉ ምንድን ነው? (T-32)፣ ዓለምን እየተቆጣጠረ ያለው ማን ነው? (T-33)፣ መከራ የማይኖርበት ጊዜ ይመጣል? (T-34)፣ የሞቱ ሰዎች እንደገና በሕይወት መኖር ይችላሉ? (T-35)፣ የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? (T-36)።
◼ ከመስከረም ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጡት የሕዝብ ንግግር “የአምላክን መንገድ መከተል ጠቃሚ ነው?” የሚል ርዕስ ያለው ይሆናል።