ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፍጥረት 18-19
“የምድር ሁሉ ዳኛ” በሰዶምና በገሞራ ላይ የጥፋት ፍርድ በየነ
ይሖዋ በሰዶም እና በገሞራ ላይ ከወሰደው እርምጃ ምን እንማራለን?
ይሖዋ ክፋትን ለዘላለም አይታገሥም
ከመጪው ጥፋት የሚተርፉት የአምላክን ፈቃድ ለማስተዋልና ለመፈጸም ጥረት የሚያደርጉ ሰዎች ናቸው።—ሉቃስ 17:28-30
ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘በዚህ ክፉ ዓለም ውስጥ የሚፈጸመውን ዓይን ያወጣ ምግባር ስመለከት እሳቀቃለሁ?’ (2ጴጥ 2:7) ‘በዕለት ተዕለት ሕይወቴ የማከናውናቸው ነገሮች የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ ከሁሉ የላቀ ቦታ እንደምሰጥ ያሳያሉ?’