ከሰኔ 22-28
ዘፀአት 1–3
መዝሙር 7 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“መሆን የምፈልገውን እሆናለሁ”፦ (10 ደቂቃ)
[የዘፀአት መጽሐፍ ማስተዋወቂያ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት።]
ዘፀ 3:13—ሙሴ ይሖዋ የሚለው ስም የሚወክለውን አካል በተመለከተ ይበልጥ ማወቅ ፈልጎ ነበር (w13 3/15 25 አን. 4)
ዘፀ 3:14—ይሖዋ ዓላማውን ለመፈጸም ሲል መሆን የሚያስፈልገውን ሁሉ ይሆናል (kr 43 ሣጥን)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (10 ደቂቃ)
ዘፀ 2:10—የፈርዖን ሴት ልጅ ሙሴን ወስዳ አሳድጋዋለች ብሎ ማመን ምክንያታዊ የሆነው ለምንድን ነው? (g04 4/8 6 አን. 5)
ዘፀ 3:1—ዮቶር ምን ዓይነት ካህን ነበር? (w04 3/15 24 አን. 4)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ይሖዋ አምላክን፣ የመስክ አገልግሎትን ወይም ሌሎች ነገሮችን በተመለከተ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ዘፀ 2:11-25 (th ጥናት 11)
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
መመሥከር፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በውይይት ናሙናው ጀምር። በክልላችሁ ለተለመደ የተቃውሞ ሐሳብ ምላሽ ስጥ። (th ጥናት 16)
ተመላልሶ መጠየቅ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በውይይት ናሙናው ጀምር። ከዚያም የቤቱ ባለቤት ያነሳውን ርዕሰ ጉዳይ የሚዳስስ በቅርቡ የወጣ መጽሔት አበርክት። (th ጥናት 12)
ንግግር፦ (5 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) w02 6/15 11 አን. 1-4—ጭብጥ፦ ከግብፅ ሀብት የሚልቅ ነገር። (th ጥናት 13)
ክርስቲያናዊ ሕይወት
የይሖዋ ወዳጅ ሁን—የይሖዋ ስም፦ (6 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ቪዲዮውን አጫውት። ከዚያም ከተቻለ አስቀድመህ የመረጥካቸውን ጥቂት ልጆች ወደ መድረኩ እንዲወጡ ካደረግክ በኋላ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቃቸው፦ የይሖዋ ስም ትርጉም ምንድን ነው? ይሖዋ ምን ነገሮችን ፈጥሯል? ይሖዋ ሊረዳችሁ የሚችለው እንዴት ነው?
መለኮታዊው ስም በስካንዲኔቪያ ከፍ ከፍ አለ፦ (9 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ቪዲዮውን አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦ ከ16ኛው ክፍለ ዘመን በፊት መለኮታዊው ስም በብዙዎች ዘንድ የማይታወቀው ለምን ነበር? ይሖዋ የሚለው ስም በስካንዲኔቪያ ጥቅም ላይ መዋል የጀመረው እንዴት ነው? አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስን ከፍ አድርጋችሁ የምትመለከቱት ለምንድን ነው?
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) jy ምዕ. 111 አን. 10-21
የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
መዝሙር 150 እና ጸሎት