ክርስቲያናዊ ሕይወት
ይሖዋ ስደትን ወደ ምሥክርነት ይቀይራል
ብዙውን ጊዜ የአሳዳጆቻችን ዓላማ የስብከቱን ሥራ ማስቆም ነው። ይሁንና እንዲህ ባለው ከባድ ሁኔታ ውስጥ ታማኝነታችንን መጠበቃችን ግሩም ምሥክርነት ይሰጣል።
ከወንድም ዲሚትሪ ሚኻይሎቭ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ወንድም ሚኻይሎቭ ምን ዓይነት ስደት ደርሶበታል?
ወንድም ሚኻይሎቭ እንዲጸና ይሖዋ የረዳው እንዴት ነው?
ይሖዋ በወንድም ሚኻይሎቭ ላይ የደረሰውን ስደት ለሌሎች እስረኞች ምሥክርነት ለመስጠት የተጠቀመበት እንዴት ነው?