የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb21 ግንቦት ገጽ 5
  • ቁልፍ ነጥቦችን በምሳሌ ማስረዳት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቁልፍ ነጥቦችን በምሳሌ ማስረዳት
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ትምህርት አዘል ምሳሌዎች
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • በጸሎት አማካኝነት የይሖዋን እርዳታ ተቀበሉ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • የአምላክን ቃል ተጠቀሙ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • ጥያቄዎችን ተጠቀሙ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
mwb21 ግንቦት ገጽ 5
አንዲት እናትና ሴት ልጇ፣ በአካባቢው ያሉትን ወፎችና አበቦች ትክ ብለው እየተመለከቱ ኢየሱስ በተራራው ላይ የሚሰጠውን ስብከት ሲያዳምጡ።

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር | በአገልግሎት የምታገኙትን ደስታ አሳድጉ

ቁልፍ ነጥቦችን በምሳሌ ማስረዳት

ተመላልሶ መጠየቅ ስናደርግም ሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ስናስጠና፣ የምናነጋግራቸው ሰዎች ቁልፍ ነጥቦችን እንዲያስተውሉ መርዳት ያስፈልገናል። እነዚህን ቁልፍ ነጥቦች ለማስረዳት ምሳሌ መጠቀማችን የሰዎችን ልብ ለመንካትና ትምህርቱን እንዲያስታውሱት ለመርዳት ያስችለናል።

ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ ወይም ጥናት ለመምራት ስትዘጋጁ በምሳሌ ልታስረዱ የምትፈልጓቸውን ነጥቦች ምረጡ፤ የምትመርጧቸው ነጥቦች ቁልፍ ነጥቦች እንጂ ዝርዝር ሐሳቦች መሆን የለባቸውም። ከዚያም በዕለት ተዕለት ሕይወት ላይ የተመሠረቱ ቀላል ምሳሌዎችን ምረጡ። (ማቴ 5:14-16፤ ማር 2:21፤ ሉቃስ 14:7-11) የግለሰቡን አስተዳደግ ወይም የኋላ ታሪክ እንዲሁም የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን ግምት ውስጥ አስገቡ። (ሉቃስ 5:2-11፤ ዮሐ 4:7-15) ግለሰቡ ልታስረዱት የፈለጋችሁት ነጥብ ገብቶት ፊቱ በደስታ ሲፈካ ስታዩ እናንተም ትደሰታላችሁ።

ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—ክህሎታችሁን አሻሽሉ—ቁልፍ ነጥቦችን በምሳሌ ማስረዳት የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ‘ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—ክህሎታችሁን አሻሽሉ—ቁልፍ ነጥቦችን በምሳሌ ማስረዳት’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ምስል። ጄድ ኒታን ጥያቄ ስትጠይቃት።

    ጥናቶች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ለመረዳት እገዛ የሚያስፈልጋቸው ለምን ሊሆን ይችላል?

  • ‘ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—ክህሎታችሁን አሻሽሉ—ቁልፍ ነጥቦችን በምሳሌ ማስረዳት’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ምስል። ኒታ ለጄድ አንድ ምሳሌ ስትነግራት።

    ኒታ በሮም 5:12 ላይ የሚገኘውን እውነት በምሳሌ ያስረዳችው እንዴት ነው?

  • ‘ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—ክህሎታችሁን አሻሽሉ—ቁልፍ ነጥቦችን በምሳሌ ማስረዳት’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ምስል። ኒታ ለጄድ አንድ ቪዲዮ ስታሳያት።

    ጥሩ ምሳሌዎች ልብ የመንካት ኃይል አላቸው

    ጥሩ ምሳሌ በምናነጋግረው ሰው ላይ ምን ውጤት ይኖረዋል?

  • በአገልግሎታችን ላይ ድርጅቱ ያዘጋጃቸውን ቪዲዮዎችና ሌሎች የማስተማሪያ መሣሪያዎች መጠቀም ያለብን ለምንድን ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ