በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር | በአገልግሎት የምታገኙትን ደስታ አሳድጉ
የሌሎችን ስሜት መረዳት
የሌሎችን ስሜት መረዳት ሲባል የሰዎችን አመለካከት፣ ስሜት፣ ከፍ አድርገው የሚመለከቷቸውን ነገሮችና የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ማወቅ ማለት ነው። ይህ ባሕርይ ሌሎችን ለመርዳት ካለን ልባዊ ፍላጎት የሚመነጭ ነው፤ የሌሎችን ስሜት ለመረዳት ጥረት ስናደርግ ሰዎች ይህን ማስተዋል አይከብዳቸውም። በአገልግሎት ላይ የሌሎችን ስሜት ለመረዳት ጥረት ስናደርግ የይሖዋን ፍቅርና አሳቢነት እናንጸባርቃለን፤ ይህ ደግሞ ሰዎች ወደ እሱ እንዲሳቡ ያደርጋል።—ፊልጵ 2:4
የሌሎችን ስሜት መረዳት አንድን የማስተማር ክህሎት የመጠቀም ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ በምናዳምጥበትና በምንናገርበት መንገድ እንዲሁም በምናሳየው ባሕርይ፣ በአካላዊ መግለጫችንና በፊታችን ገጽታ ላይ ይታያል። ግለሰቡ፣ እሱን ለመርዳት ከልባችን እንደምንፈልግ እንዲያውቅ ማድረግ ይኖርብናል። የግለሰቡን ትኩረት የሚስቡትን ነገሮች፣ የሚያምንባቸውን ነገሮችና ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ ጥረት እናደርጋለን። የሚጠቅመውን ሐሳብ እንነግረዋለን እንዲሁም ተግባራዊ እርዳታ እንሰጠዋለን፤ ሆኖም ለውጥ እንዲያደርግ አንጫነውም። ሰዎች እነሱን ለመርዳት ለምናደርገው ጥረት አዎንታዊ ምላሽ ሲሰጡ በአገልግሎት የምናገኘው ደስታ ይጨምራል።
ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—ክህሎታችሁን አሻሽሉ—የሌሎችን ስሜት መረዳት የሚለውን አጭር ድራማ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ጄድ አርፍዳ ስትመጣ ኒታ ስሜቷን እንደተረዳችላት ያሳየችው እንዴት ነው?
ጄድ በጣም ከመወጠሯ የተነሳ ማጥናት እንደማትችል ስትናገር ኒታ ስሜቷን እንደተረዳችላት ያሳየችው እንዴት ነው?
የሌሎችን ስሜት ለመረዳት ጥረት ማድረጋችን ሰዎች ወደ ይሖዋ እንዲሳቡ ያደርጋል
ጄድ የተደራጀች እንዳልሆነች ስትናገር ኒታ ስሜቷን እንደተረዳችላት ያሳየችው እንዴት ነው?