ክርስቲያናዊ ሕይወት
“ፍቅር . . . አይታበይም”
ፍቅር ትሕትና እንድናሳይ ይረዳናል። (1ቆሮ 13:4) ለወንድሞቻችን ፍቅር ካለን ራሳችንን ከእነሱ ከፍ አድርገን አንመለከትም። የሌሎችን መልካም ጎን እናያለን፤ እንዲሁም ችሎታችንን እነሱን ለመርዳት እንጠቀምበታለን። (ፊልጵ 2:3, 4) እንዲህ ያለውን ፍቅር ይበልጥ ባሳየን መጠን ይሖዋም ፈቃዱን ለማድረግ ይበልጥ ይጠቀምብናል።
ፍቅር የሚያደርጋቸውና የማያደርጋቸው ነገሮች—አይታበይም የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
አቢሴሎም የትኞቹ ስጦታዎች ነበሩት?
ስጦታውን ያለአግባብ የተጠቀመበት እንዴት ነው?
እንዳንታበይ ምን ይረዳናል?—ገላ 5:26