ክርስቲያናዊ ሕይወት
የጸሎታችሁን መልስ ለማስተዋል ጥረት ታደርጋላችሁ?
መጽሐፍ ቅዱስ ይሖዋ የመለሳቸውን በርካታ ጸሎቶች ይዟል። የአምላክ አገልጋዮች ይሖዋ ጭንቀታቸውን ሰምቶ እንደረዳቸው ሲመለከቱ እምነታቸው እንደተጠናከረ ምንም ጥያቄ የለውም። በመሆኑም ወደ ይሖዋ በምንጸልይበት ወቅት የምንፈልገውን ነገር ለይተን መጥቀሳችን ከዚያም ይሖዋ የሚሰጠንን መልስ ለማስተዋል ጥረት ማድረጋችን አስፈላጊ ነው። ይሖዋ የሚሰጠን መልስ ከጠየቅነው የተለየ ወይም የበለጠ ሊሆን እንደሚችል አስታውሱ። (2ቆሮ 12:7-9፤ ኤፌ 3:20) ይሖዋ ጸሎታችንን የሚመልስልን በምን መንገድ ሊሆን ይችላል?
ያጋጠመንን ችግር ለመቋቋም የሚያስችል አካላዊ፣ ስሜታዊ ወይም መንፈሳዊ ጥንካሬ በመስጠት።—ፊልጵ 4:13
ጥሩ ውሳኔ ለማድረግ የሚያስችል ጥበብ በመስጠት።—ያዕ 1:5
ለተግባር የሚያነሳሳ ፍላጎት እንዲያድርብንና ኃይል እንድናገኝ በማድረግ።—ፊልጵ 2:13
በምንጨነቅበት ጊዜ እንድንረጋጋ በመርዳት።—ፊልጵ 4:6, 7
ሌሎች ቁሳዊም ሆነ ስሜታዊ ድጋፍ እንዲሰጡን በማድረግ።—1ዮሐ 3:17, 18
ይሖዋ “ጸሎት ሰሚ” ነው የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ባለብን የጤና እክል ምክንያት ማከናወን የምንችለው ነገር የተገደበ ከሆነ የወንድም ሺሚዙ ተሞክሮ የሚያበረታታን እንዴት ነው?
የወንድም ሺሚዙን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው?