የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb23 ጥር ገጽ 5
  • በአምላክ ቃል ላይ ያላችሁን እምነት አጠናክሩ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በአምላክ ቃል ላይ ያላችሁን እምነት አጠናክሩ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በይሖዋ እንደምንታመን የሚያሳዩ ውሳኔዎች
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ ማንበብ ጥበብ ለማግኘት ይረዳል
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ልብ ብላችሁ አዳምጡ
    የ2025-2026 የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም—የወረዳ የበላይ ተመልካች የሚገኝበት
  • የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ልብ ብላችሁ አዳምጡ
    የ2025-2026 የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም—የቅርንጫፍ ቢሮ ተወካይ የሚገኝበት
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
mwb23 ጥር ገጽ 5
ፎቶግራፎች፦ አንዲት ወጣት እህት መጽሐፍ ቅዱስን ስታነብና ስታጠና። 1. የመጽሐፍ ቅዱስ ባለታሪኮችን በጊዜ ሰሌዳ ላይ ስታሰፍር። 2. jw.org ላይ ለጥናት የተዘጋጀውን “አዲስ ዓለም ትርጉም” ስታነብ። 3. በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱ ቦታዎችን የሚያሳይ ካርታ ስትመለከት። 4. ሊቀ ካህናቱን ሥላ በልብሶቹ ላይ ምልክት ስታደርግ።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በአምላክ ቃል ላይ ያላችሁን እምነት አጠናክሩ

የአምላክ ቃል ሕይወታችንን ይለውጣል። (ዕብ 4:12) ይሁንና በውስጡ ከሚገኘው መመሪያና ምክር ጥቅም ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥ ‘የአምላክ ቃል’ መሆኑን ማመን ይኖርብናል። (1ተሰ 2:13) ታዲያ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለንን እምነት ማጠናከር የምንችለው እንዴት ነው?

በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን አንብቡ። በምታነቡበት ጊዜ መጽሐፉን ያስጻፈው ይሖዋ እንደሆነ የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ለማስተዋል ሞክሩ። ለአብነት ያህል፣ የምሳሌ መጽሐፍን በመመርመር በውስጡ ያለው ምክር ጊዜ የማይሽረው መሆኑን አስተውሉ።—ምሳሌ 13:20፤ 14:30

የጥናት ፕሮጀክት ጀምሩ። መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ መሪነት የተጻፈ መጽሐፍ መሆኑን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ፈልጉ። የምርምር መርጃ መሣሪያ ለይሖዋ ምሥክሮች በተባለው መጽሐፍ ላይ “መጽሐፍ ቅዱስ” በሚለው ሥር “በአምላክ መንፈስ መሪነት ተጽፏል” የሚለውን ተመልከቱ። በተጨማሪም በአዲስ ዓለም ትርጉም ላይ ተጨማሪ መረጃ ሀ3 ሥር የሚገኘውን ሐሳብ በመመርመር የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት እንዳልተለወጠ ያላችሁን እምነት ማጠናከር ትችላላችሁ።

እምነት እንዲኖረን ያደረገን ምንድን ነው?—በአምላክ ቃል ላይ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • በካርናክ፣ ግብፅ ባለው ቤተ መቅደስ ግድግዳ ላይ የተገኘው ነገር የአምላክ ቃል እውነተኛ መሆኑን ያረጋገጠው እንዴት ነው?

  • የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት እንዳልተለወጠ እንዴት እናውቃለን?

  • መጽሐፍ ቅዱስ እስከ ዘመናችን ተጠብቆ መቆየቱ የአምላክ ቃል መሆኑን የሚያረጋግጠው እንዴት ነው?—ኢሳይያስ 40:8⁠ን አንብብ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ