የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb23 መስከረም ገጽ 7
  • ለይሖዋ ሕዝቦች ጥቅም የቆሙ እረኞች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለይሖዋ ሕዝቦች ጥቅም የቆሙ እረኞች
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘ሽማግሌዎችን ጥራ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2025
  • ለኃጢአተኞች ፍቅርና ምሕረት ማሳየት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
  • ወንድሞች—የጉባኤ ሽማግሌ ለመሆን እየተጣጣራችሁ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
  • በይሖዋ እንደምንታመን የሚያሳዩ ውሳኔዎች
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
mwb23 መስከረም ገጽ 7

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ለይሖዋ ሕዝቦች ጥቅም የቆሙ እረኞች

ብዙዎች ሥልጣን ላይ ላሉ ሰዎች አሉታዊ አመለካከት አላቸው። ደግሞም አይፈረድባቸውም። የሰው ልጆች ለበርካታ ዘመናት ሥልጣናቸውን አላግባብ በመጠቀም የራሳቸውን ጥቅም ሲያራምዱ ኖረዋል። (ሚክ 7:3) በጉባኤ ውስጥ ያሉ ሽማግሌዎች ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ለይሖዋ ሕዝቦች ጥቅም እንዲቆሙ ሥልጠና በማግኘታቸው ምንኛ አመስጋኞች ነን!—አስ 10:3፤ ማቴ 20:25, 26

በዓለም ውስጥ ሥልጣን ላይ ካሉ ሰዎች በተቃራኒ ሽማግሌዎች የበላይ ተመልካች ለመሆን የሚጣጣሩት ለይሖዋና ለሕዝቡ ፍቅር ስላላቸው ነው። (ዮሐ 21:16፤ 1ጴጥ 5:1-3) በኢየሱስ አመራር ሥር ያሉት እነዚህ እረኞች እያንዳንዱ አስፋፊ በይሖዋ ቤተሰብ ውስጥ ቦታ እንዳለው እንዲሰማውና ወደ እሱ እንዲቀርብ ለመርዳት ጥረት ያደርጋሉ። ለይሖዋ በጎች መንፈሳዊ እርዳታ ለመስጠት እንዲሁም ድንገተኛ የጤና እክል ወይም የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥማቸው እገዛ ለማድረግ ፈጣኖች ናቸው። እርዳታ የሚያስፈልግህ ከሆነ፣ ቅድሚያውን ወስደህ በጉባኤህ ውስጥ ያለን አንድ ሽማግሌ ለምን አታነጋግርም?—ያዕ 5:14

“መንጋውን የሚንከባከቡ እረኞች” ከሚለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። አንድ ሽማግሌ ኤልያስን በፈገግታ አቅፎ ሰላም ሲለው።

መንጋውን የሚንከባከቡ እረኞች የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ማሪያና ሽማግሌዎች ከሰጧት እርዳታ የተጠቀመችው እንዴት ነው?

  • ኤልያስ ሽማግሌዎች ከሰጡት እርዳታ የተጠቀመው እንዴት ነው?

  • ቪዲዮውን ከተመለከትክ በኋላ ሽማግሌዎች ስለሚያከናውኑት ሥራ ምን ተሰማህ?

የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙህ ቅድሚያውን ወስደህ ሽማግሌዎችን አነጋግር፦

  • አድራሻ ስትቀይር

  • ከባድ ፈተና ሲያጋጥምህ

  • ረዘም ላለ ጊዜ አካባቢህን ለቀህ የምትሄድ ከሆነ

  • ከባድ የጤና እክል ሲያጋጥምህ ወይም ሆስፒታል መተኛት ሲኖርብህ

  • ከባድ ኃጢአት ከፈጸምክ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ