ከሚያዝያ 22-28
መዝሙር 32–33
መዝሙር 103 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. ከባድ ኃጢአት ከፈጸምን መናዘዝ ያለብን ለምንድን ነው?
(10 ደቂቃ)
ዳዊት ኃጢአቱን ለመደበቅ በሞከረበት ወቅት በጭንቀት ተውጦ ነበር፤ ይህ የሆነው ከቤርሳቤህ ጋር ምንዝር በፈጸመበት ወቅት ሊሆን ይችላል (መዝ 32:3, 4፤ w93 3/15 9 አን. 7)
ዳዊት ኃጢአቱን ለይሖዋ በመናዘዙ ይቅር ተብሏል (መዝ 32:5፤ cl 262 አን. 8)
ዳዊት የይሖዋን ይቅርታ ካገኘ በኋላ እፎይታ ተሰምቶታል (መዝ 32:1፤ w01 6/1 30 አን. 1)
ከባድ ኃጢአት ከፈጸምን ስህተታችንን በትሕትና አምነን በመቀበልና ይሖዋን ይቅርታ በመጠየቅ ኃጢአታችንን ለእሱ ልንናዘዝ ይገባል። የሽማግሌዎችን እርዳታም መጠየቅ ይኖርብናል፤ እነሱም እንደገና በመንፈሳዊ ጤናማ እንድንሆን ይረዱናል። (ያዕ 5:14-16) በውጤቱም ከይሖዋ ዘንድ የመታደስ ዘመን ይመጣልናል።—ሥራ 3:19
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
መዝ 33:6—ከይሖዋ አፍ የሚወጣው “መንፈስ” ምንድን ነው? (w06 5/15 20 አን. 1)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) መዝ 33:1-22 (th ጥናት 11)
4. ትሕትና—ጳውሎስ ምን አድርጓል?
(7 ደቂቃ) ውይይት። ቪዲዮውን አጫውት፤ ከዚያም lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 1-2 ላይ ተወያዩ።
5. ትሕትና—ጳውሎስን ምሰል
(8 ደቂቃ) lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 3-5 እና “ተጨማሪ ጥቅሶች” ላይ የተመሠረተ ውይይት።
መዝሙር 74
6. ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ
(15 ደቂቃ)
7. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 8 አን. 22-24፣ በገጽ 67 ላይ ያለው ሣጥን