ከሚያዝያ 29–ግንቦት 5
መዝሙር 34–35
መዝሙር 10 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. “ይሖዋን ሁልጊዜ አወድሰዋለሁ”
(10 ደቂቃ)
ዳዊት በመከራ ውስጥ ሆኖም ይሖዋን አወድሷል (መዝ 34:1፤ w07 3/1 22 አን. 11)
ዳዊት በራሱ ሳይሆን በይሖዋ ተኩራርቷል (መዝ 34:2-4፤ w07 3/1 22 አን. 13)
ዳዊት ያቀረበው ውዳሴ ባልንጀሮቹን አበረታቷል (መዝ 34:5፤ w07 3/1 23 አን. 15)
ዳዊት ከአቢሜሌክ እጅ ከተረፈ በኋላ በሳኦል ላይ ቅሬታ ያላቸው 400 ሰዎች ከእሱ ጋር ለመሆን ወደ ምድረ በዳ መጥተዋል። (1ሳሙ 22:1, 2) ዳዊት ይህን መዝሙር ያቀናበረው እንደ እነሱ ያሉ ሰዎችን በአእምሮው ይዞ ሊሆን ይችላል።—መዝ 34 አናት ላይ ያለው መግለጫ
ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘በቀጣዩ የጉባኤ ስብሰባ ላይ ከሌሎች ጋር ስነጋገር ይሖዋን ማወደስ የምችለው እንዴት ነው?’
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
መዝ 35:19—ዳዊት ‘ጠላቶቼ እንዲጠቃቀሱብኝ አትፍቀድ’ ሲል ምን ማለቱ ነበር? (w06 5/15 20 አን. 2)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) መዝ 34:1-22 (th ጥናት 5)
4. ውይይት መጀመር
(2 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ምሥክርነት መስጠት ከመቻልህ በፊት ውይይታችሁ ይደመደማል። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 4)
5. ተመላልሶ መጠየቅ
(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። (lmd ምዕራፍ 2 ነጥብ 4)
6. እምነታችንን ማብራራት
መዝሙር 59
7. በስብሰባዎች ላይ ይሖዋን ማወደስ የምንችልባቸው ሦስት መንገዶች
(15 ደቂቃ) ውይይት።
የጉባኤ ስብሰባዎች ይሖዋን ማወደስ የምንችልባቸው ግሩም አጋጣሚዎች ይሰጡናል። ሦስት መንገዶችን እስቲ እንመልከት።
ስንጨዋወት፦ ከሌሎች ጋር ስትጨዋወቱ ስለ ይሖዋ ጥሩነት ተናገሩ። (መዝ 145:1, 7) የሰማችሁት ወይም ያነበባችሁት ጠቃሚ ነጥብ አለ? አገልግሎት ላይ ጥሩ ተሞክሮ አግኝታችኋል? በንግግር ወይም በድርጊት ያበረታታችሁ ሰው አለ? አስደናቂ የፍጥረት ሥራ ተመልክታችኋል? እነዚህ ነገሮች ሁሉ የይሖዋ ስጦታዎች ናቸው። (ያዕ 1:17) ከሌሎች ጋር የምትጨዋወቱበት ጊዜ እንዲኖራችሁ ስብሰባው ከመጀመሩ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ድረሱ።
ሐሳብ ስንሰጥ፦ በእያንዳንዱ ስብሰባ ላይ ቢያንስ አንድ ሐሳብ ለመስጠት ጥረት አድርጉ። (መዝ 26:12) በጥያቄው፣ በተጨማሪ ነጥቦች፣ በጥቅሶች፣ በሥዕሎች ወይም ትምህርቱን ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ሐሳብ መስጠት ትችላላችሁ። ሌሎችም እጃቸውን ማውጣታቸው ስለማይቀር ከአንድ በላይ ሐሳብ ተዘጋጁ። በ30 ሴኮንድ ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሐሳብ የምትሰጡ ከሆነ ብዙዎች ‘የውዳሴ መሥዋዕት ለአምላክ ማቅረብ’ ይችላሉ።—ዕብ 13:15
ስንዘምር፦ የመንግሥቱን መዝሙሮች በግለት ዘምሩ። (መዝ 147:1) በተለይ ጉባኤያችሁ ትልቅ ከሆነ በእያንዳንዱ ስብሰባ ላይ ሐሳብ የመስጠት አጋጣሚ አታገኙ ይሆናል፤ ሆኖም ሁልጊዜም መዝሙር መዘመር ትችላላችሁ። የመዘመር ችሎታ እንደሌላችሁ ቢሰማችሁም እንኳ አቅማችሁ የፈቀደውን ስታደርጉ ይሖዋ እጅግ ይደሰታል! (2ቆሮ 8:12) መዝሙሮቹን ቤታችሁ በመለማመድ አስቀድማችሁ መዘጋጀት ትችላላችሁ።
ታሪካችን—ከየት ወዴት?—የመዝሙር ስጦታ፣ ክፍል 1 የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦
በድርጅታችን ዘመናዊ ታሪክ መጀመሪያ አካባቢ ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር ለመዘመር ትልቅ ቦታ እንደምንሰጥ ያሳየነው እንዴት ነው?
8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 9 አን. 1-7፣ የክፍል 3 ማስተዋወቂያ እና በገጽ 70 ላይ ያለው ሣጥን