የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb24 ሐምሌ ገጽ 10-16
  • ከነሐሴ 5-11

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከነሐሴ 5-11
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
mwb24 ሐምሌ ገጽ 10-16

ከነሐሴ 5-11

መዝሙር 70–72

መዝሙር 59 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. “ለቀጣዩ ትውልድ” ስለ አምላክ ኃይል ተናገሩ

(10 ደቂቃ)

ዳዊት በወጣትነቱ የይሖዋን ጥበቃ አግኝቷል (መዝ 71:5፤ w99 9/1 18 አን. 17)

ዳዊት በስተ እርጅናው የይሖዋን ድጋፍ አጣጥሟል (መዝ 71:9፤ g04 10/8 23 አን. 3)

ዳዊት ተሞክሮውን በመናገር ወጣቶችን አበረታቷል (መዝ 71:17, 18፤ w14 1/15 23 አን. 4-5)

ባለፈው ሳምንት ስብሰባ ላይ “ለቤተሰብ አምልኮ ምሽት የሚጠቅሙ ምክሮች” በሚለው ክፍል ላይ የታየው ቤተሰብ። በቤተሰብ አምልኳቸው ላይ አንድን አረጋዊ ባልና ሚስት ጋብዘው ባልና ሚስቱ ፎቶ እያሳዩአቸው ተሞክሮ ሲነግሯቸው በደስታ ሲያዳምጡ።

ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘በቤተሰብ አምልኳችን ላይ በጉባኤያችን ውስጥ ካሉት ለረጅም ጊዜ ይሖዋን ያገለገሉ ክርስቲያኖች መካከል ለማን ቃለ መጠይቅ ማድረግ እችላለሁ?’

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 72:8—ይሖዋ በዘፍጥረት 15:18 ላይ ለአብርሃም የገባው ቃል በንጉሥ ሰለሞን የግዛት ዘመን ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነው? (it-1 768)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 71:1-24 (th ጥናት 5)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ መከራከር ሲጀምር ውይይቱን አዎንታዊ በሆነ መንገድ አቁም። (lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 5)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ከአንድ ዘመድህ ጋር ቀደም ሲል የጀመርከውን ውይይት ቀጥል፤ ግለሰቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለመጀመር እያመነታ ነው። (lmd ምዕራፍ 8 ነጥብ 4)

6. እምነታችንን ማብራራት

(5 ደቂቃ) ንግግር። ijwfq 49—ጭብጥ፦ የይሖዋ ምሥክሮች ከሚያምኑባቸው ነገሮች አንዳንዶቹን የቀየሩት ለምንድን ነው? (th ጥናት 17)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 76

7. ለቤተሰብ አምልኮ የሚሆኑ ሐሳቦች

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ቀደም ሲል የታዩት ቤተሰቦች ቆመው የመንግሥቱን መዝሙር ሲለማመዱ።
ቤተሰቡ JW ብሮድካስቲንግ ሲመለከት።
ከልጆቹ አንዷ በቤተሰብ አምልኮ ላይ የልምምድ ፕሮግራም ሲያደርጉ ለእናቷ ስትመልስላት።

የቤተሰብ አምልኮ፣ ልጆች ስለ “ይሖዋ ተግሣጽና ምክር” የሚማሩበት ግሩም አጋጣሚ ይፈጥራል። (ኤፌ 6:4) መማር ሥራ ይጠይቃል፤ ሆኖም በተለይ ልጆች ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ጉጉት እያዳበሩ ሲሄዱ መማር አስደሳች ሊሆንላቸው ይችላል። (ዮሐ 6:27፤ 1ጴጥ 2:2) ወላጆች የቤተሰብ አምልኳቸውን ትምህርት ሰጪና አስደሳች እንዲያደርጉ ለመርዳት የተዘጋጀውን “ለቤተሰብ አምልኮ የሚሆኑ ሐሳቦች” የሚለውን ሣጥን ከልስ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ከእነዚህ ሐሳቦች መካከል የትኛውን መሞከር ትፈልጋላችሁ?

  • ጠቃሚ ሆኖ ያገኛችሁት ሌላ ነገር አለ?

ለቤተሰብ አምልኮ የሚሆኑ ሐሳቦች

መጽሐፍ ቅዱስ፦

  • ሳምንታዊውን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የድምፅ ቅጂ አዳምጡ፤ ወይም ተከፋፍላችሁ ጮክ ብላችሁ አንብቡት። እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል የተለያዩ ገጸ ባሕርያትን ወክሎ ሊያነብ ይችላል

  • በሳምንታዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ላይ ተመሥርታችሁ ጥያቄዎች አዘጋጁ። ሁሉም የቤተሰብ አባላት አንድ አንድ ጥያቄ መርጠው ምርምር ያደርጋሉ። ከዚያም ያገኙትን ሐሳብ ያካፍላሉ

  • አንድ ጥያቄ ወይም ሁኔታ አንሱ፤ ከዚያም ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወትን ተጠቅማችሁ ከጉዳዩ ጋር በተያያዙ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ላይ ምርምር አድርጉ

  • አንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ በትወና አሳዩ

  • በየሳምንቱ የተለያዩ ጥቅሶችን የያዘ ካርድ አዘጋጁ፤ ለምሳሌ ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ በተባለው ብሮሹር ተጨማሪ መረጃ ሀ ላይ ያሉትን ጥቅሶች መጠቀም ትችላላችሁ፤ ከዚያም ጥቅሱን በቃላችሁ ለመያዝ ጥረት አድርጉ። ባለፉት ሳምንታት ያዘጋጃችኋቸውን ካርዶች ከልሱ

  • ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን መጽሐፍ የተወሰነ ክፍል አጥኑ

  • የቤተሰቡ አባላት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች በሚለው ክፍል ሥር “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው” ወይም “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው” በሚሉት ዓምዶች ውስጥ ካሉት ርዕሶች በአንዱ ላይ ሪፖርት እንዲያቀርቡ መድቡ

ስብሰባዎች፦

  • ከጉባኤ ስብሰባ ላይ የተወሰነውን ክፍል ተዘጋጁ

  • መልስ ተዘጋጅታችሁ ተለማመዱ። የመልሳችሁን ርዝመት ገምግሙ

  • የመንግሥቱን መዝሙሮች ተለማመዱ

  • በቀጣዩ ስብሰባ ላይ ከስብሰባው በፊት ወይም በኋላ አንድን ሰው ለማበረታታት ምን ማለት እንደምትችሉ ተወያዩ፤ እንዲሁም ተለማመዱ

  • በቅርቡ የምታቀርቡትን የተማሪ ክፍል በቤተሰባችሁ ፊት ተለማመዱ

አገልግሎት፦

  • ከቤት ወደ ቤት ለማገልገል ተዘጋጁ

  • ለተመላልሶ መጠየቆቻችሁ ተዘጋጁ

  • መደበኛ ባልሆነ መንገድ ለመመሥከር፣ አንድን ሁኔታ መርጣችሁ ጭውውት መጀመር የምትችሉት እንዴት እንደሆነ ተለማመዱ

  • በመታሰቢያው በዓል ሰሞን አሊያም ደግሞ ከሥራ ወይም ከትምህርት እረፍት ስታገኙ አገልግሎታችሁን ለማስፋት የትኞቹን ግቦች ማውጣት እንደምትችሉ ተወያዩ

ለቤተሰቡ የሚያስፈልጉ ነገሮች፦

  • የቤተሰባችሁን አባላት ያጋጠሙ ወይም ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሁኔታዎችን እንዴት መያዝ እንደምትችሉ ተለማመዱ፤ ለምሳሌ ከገለልተኝነት፣ ከጉልበተኞች ጥቃት፣ ከፍቅር ግንኙነት ወይም ከበዓላት ጋር የተያያዙ ሁኔታዎች ሊሆኑ ይችላሉ

  • ወላጆች እንደ ልጅ፣ ልጆች ደግሞ እንደ ወላጅ የሚሆኑበት የልምምድ ፕሮግራም አዘጋጁ። ልጆቹ ስለ ርዕሰ ጉዳዩ ምርምር አድርገው ወላጆቻቸውን ለማስረዳት ይሞክራሉ

ተጨማሪ ሐሳቦች፦

  • አንድን የ​JW ብሮድካስቲንግ ፕሮግራም ተመልክታችሁ ተወያዩበት

  • jw.org ላይ የሚገኝ ርዕስ አንብቡ ወይም ቪዲዮ ተመልከቱ፤ ከዚያም ተወያዩበት

  • jw.org ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች በሚለው ክፍል ሥር “ታዳጊዎች እና ወጣቶች” ወይም “ልጆች” በሚሉት ዓምዶች ውስጥ ያሉትን ነገሮች አጥኑ

  • በክልል ወይም በወረዳ ስብሰባ ላይ የያዛችሁትን ማስታወሻ ከልሱ

  • አንድን የፍጥረት ሥራ ተመልከቱ ወይም ምርምር አድርጉ፤ ከዚያም ስለ ይሖዋ ምን እንደሚያስተምረን ተወያዩ

  • አልፎ አልፎ እንግዶችን ጋብዛችሁ ቃለ መጠይቅ አድርጉላቸው

  • መንፈሳዊ ግቦችን አውጡ፤ እንዲሁም ግባችሁ ላይ እንዴት መድረስ እንደምትችሉ ተወያዩ

  • አንድ ፕሮጀክት አብራችሁ ሥሩ፤ ለምሳሌ ሞዴል፣ ካርታ ወይም ሰንጠረዥ ማዘጋጀት ትችላላችሁ

የቤተሰብ አምልኳችሁን ማሻሻላችሁን ቀጥሉ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • ልጆች ከሌሉ አንድ ባል የቤተሰብ አምልኮውን ለሚስቱ አስደሳች ማድረግ የሚችለው እንዴት ነው?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 13 አን. 17-24

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 123 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ