የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb24 መስከረም ገጽ 5-16
  • ከመስከረም 16-22

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከመስከረም 16-22
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
mwb24 መስከረም ገጽ 5-16

ከመስከረም 16-22

መዝሙር 85–87

መዝሙር 41 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ንጉሥ ዳዊት አጥብቆ ሲጸልይ።

1. ጸሎት ለመጽናት ይረዳናል

(10 ደቂቃ)

ደስታ እንዲሰጣችሁ ይሖዋን ጠይቁት (መዝ 86:4)

ታማኝነታችሁን ለመጠበቅ እንዲረዳችሁ ይሖዋን ጠይቁት (መዝ 86:11, 12፤ w12 5/15 25 አን. 10)

ይሖዋ ጸሎታችሁን እንደሚመልስላችሁ ተማመኑ (መዝ 86:6, 7፤ w23.05 13 አን. 17-18)


ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘መከራ ሲደርስብኝ የጸሎቴ ርዝመት ይጨምራል? ይበልጥ አዘውትሬስ እጸልያለሁ?’—መዝ 86:3

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 86:11—የዳዊት ጸሎት የሰዎችን ልብ በተመለከተ ምን ይጠቁማል? (it-1 1058 አን. 5)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 86:1–87:7 (th ጥናት 12)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ግለሰቡ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠና ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 3 ነጥብ 5)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ባለፈው ግለሰቡ አንድ ወቅታዊ ጉዳይ እንዳሳሰበው ነግሮህ ነበር፤ ግለሰቡ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠና ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 7 ነጥብ 4)

6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

(5 ደቂቃ) lff ምዕራፍ 15 ነጥብ 5። በሚቀጥለው ሳምንት አንተ ወደ ሌላ አካባቢ ብትሄድም ተማሪው ጥናቱን ማጥናት ስለሚችልበት መንገድ ተወያዩ። (lmd ምዕራፍ 10 ነጥብ 4)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 83

7. ተስፋ አትቁረጡ

(5 ደቂቃ) ውይይት።

ቪዲዮውን አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • አንዳንድ ጊዜ አገልግሎታችን ተስፋ ሊያስቆርጠን የሚችለው ለምንድን ነው?

  • ተስፋ መቁረጥ የሌለብን ለምንድን ነው?

8. ሰዎች ጥናት እንዲጀምሩ መጋበዛችሁን ቀጥሉ!

(10 ደቂቃ) ውይይት።

አንዲት እህት የታክሲ መቆሚያ ላይ ለአንዲት ሴት ስትመሠክር።
አንድ ባልና ሚስት “የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በነፃ” የሚል የምሥክርነት ጋሪ ጋ ቆመዋል፤ አንዲት ሴት በዚያ ስታልፍ ጋሪውን ታየዋለች።
አንድ ባልና ሚስት ከቤት ወደ ቤት እያገለገሉ ለአንድ ሰው “ለዘላለም በደስታ ኑር!” የተባለውን ብሮሹር ሲያበረክቱ።

በዚህ ወር እየተካሄደ ባለው ልዩ ዘመቻ ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን ብሮሹር ተጠቅመህ ጥናት አስጀምረሃል? ከሆነ በጣም ተደስተህ መሆን አለበት! ሌሎችም አንተ ባገኘኸው ውጤት ተበረታተው እንደሚሆን ምንም ጥያቄ የለውም። በሌላ በኩል ደግሞ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር ካልቻልክ ጥረትህ ከንቱ እንደሆነ ሊሰማህ ይችላል። ያገኘኸው ውጤት ተስፋ ካስቆረጠህ ምን ማድረግ ትችላለህ?

‘በትዕግሥት ራሳችንን ብቁ የአምላክ አገልጋዮች አድርገን እናቀርባለን’—ስንሰብክ የተባለውን አጭር ድራማ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • አገልግሎታችን ምንም ውጤት እንዳላስገኘ በሚሰማን ጊዜ 2 ቆሮንቶስ 6:4, 6 የሚረዳን እንዴት ነው?

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ያደረግከው ጥረት ምንም ውጤት ካላስገኘ የትኞቹን ማስተካከያዎች ማድረግ ትችላለህ?

ደስታ ማግኘታችን የተመካው ባስጀመርናቸው ወይም በምንመራቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ብዛት ላይ እንዳልሆነ አስታውስ። ከዚህ ይልቅ ደስታ የሚያስገኝልን ይሖዋ በጥረታችን እንደተደሰተ ማወቃችን ነው። (ሉቃስ 10:17-20) እንግዲያው ‘ከጌታ ጋር በተያያዘ በትጋት የምታከናውነው ሥራ ከንቱ አለመሆኑን አውቀህ’ በዚህ ልዩ ዘመቻ በሙሉ ልብህ መካፈልህን ቀጥል።—1ቆሮ 15:58

9. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 15 አን. 13-14፣ በገጽ 121 ላይ ያለው ሣጥን

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 39 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ