የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb24 መስከረም ገጽ 6-7
  • ከመስከረም 23-29

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከመስከረም 23-29
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
mwb24 መስከረም ገጽ 6-7

ከመስከረም 23-29

መዝሙር 88–89

መዝሙር 22 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. የይሖዋ አገዛዝ ከሁሉ የተሻለ ነው

(10 ደቂቃ)

የይሖዋ አገዛዝ እውነተኛ ፍትሕ ያሰፍናል (መዝ 89:14፤ w17.06 28 አን. 5)

የይሖዋ አገዛዝ እውነተኛ ደስታ ያሰፍናል (መዝ 89:15, 16፤ w17.06 29 አን. 10-11)

የይሖዋ አገዛዝ ለዘላለም ይጸናል (መዝ 89:34-37፤ w14 10/15 10 አን. 14)

ሥዕሎች፦ አንድ ወንድም የይሖዋን አገዛዝ ከዓለም አገዛዝ ጋር እያነጻጸረ ሲያሰላስል። 1. በፖለቲካዊ ሰልፍ ላይ ሰዎች ሲጨቃጨቁ። 2. ወንድሞች በጉባኤ ስብሰባ ላይ ሞቅ ያለ ሰላምታ ሲሰጣጡ።

የይሖዋ አገዛዝ የላቀ እንደሆነ ማሰላሰላችን ፖለቲካዊ ፕሮፓጋንዳ ስንሰማ ገለልተኝነታችንን እንድንጠብቅ ይረዳናል

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 89:37—ጨረቃ በምታሳየው ታማኝነት እና ሰዎች በሚያሳዩት ታማኝነት መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? (cl 281 አን. 4-5)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 89:1-24 (th ጥናት 11)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። የክርስትና እምነት ተከታይ ያልሆነን ሰው መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠና ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 5 ነጥብ 5)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። መጽሐፍ ቅዱስን የምናስጠናው እንዴት እንደሆነ አሳየው። (th ጥናት 9)

6. እምነታችንን ማብራራት

(5 ደቂቃ) ንግግር። ijwbq 181—ጭብጥ፦ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ስለ ምንድን ነው? (th ጥናት 2)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 94

7. የይሖዋ መሥፈርቶች ከሁሉ የተሻሉ ናቸው

(10 ደቂቃ) ውይይት።

ብዙ ሰዎች የፆታ ግንኙነትንና ጋብቻን አስመልክቶ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት መሥፈርቶች ምክንያታዊነት የጎደላቸውና ጊዜ ያለፈባቸው እንደሆኑ ይሰማቸዋል። የይሖዋን መሥፈርቶች መከተልህ ምንጊዜም እንደሚጠቅምህ ለራስህ አረጋግጠሃል?—ኢሳ 48:17, 18፤ ሮም 12:2

    “ያሳመኑኝ ምክንያቶች—የአምላክ መመሪያዎች ወይስ የኔ?” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ሥዕል። ኡጎ እና ክላራ።
  • ዓለም ባወጣቸው የሥነ ምግባር መሥፈርቶች መተማመን የሌለብን ለምንድን ነው? (ኤር 10:23፤ 17:9፤ 2ቆሮ 11:13-15፤ ኤፌ 4:18, 19)

  • ሥዕሎች፦ “ያሳመኑኝ ምክንያቶች—የአምላክ መመሪያዎች ወይስ የኔ?” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰዱ ሥዕሎች። 1. የ​jw.org ዓርማ የሚታይበት ታብሌት። 2. ኡጎ በባቡር እየተጓዘ በስልኩ መጽሐፍ ቅዱስ ሲያነብ። 3. ክላራ ስትጸልይ።
  • ይሖዋ ባወጣቸው የሥነ ምግባር መሥፈርቶች መተማመን ያለብን ለምንድን ነው? (ዮሐ 3:16፤ ሮም 11:33፤ ቲቶ 1:2)

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ ያወጣቸውን የሥነ ምግባር ሕጎች የማይከተሉ ሰዎች ‘የአምላክን መንግሥት እንደማይወርሱ’ ይናገራል። (1ቆሮ 6:9, 10) ይሁንና የአምላክን መሥፈርቶች ለመከተል የሚያነሳሳን ዋነኛው ምክንያት ይህ ነው?

ያሳመኑኝ ምክንያቶች—የአምላክ መመሪያዎች ወይስ የኔ? የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • አምላክ ያወጣቸው የሥነ ምግባር መሥፈርቶች ጥበቃ የሚያደርጉልን እንዴት ነው?

8. ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ

(5 ደቂቃ)

9. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 15 አን. 15-20

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 133 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ