የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb24 ኅዳር ገጽ 4-5
  • ከኅዳር 18-24

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከኅዳር 18-24
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
mwb24 ኅዳር ገጽ 4-5

ከኅዳር 18-24

መዝሙር 107–108

መዝሙር 7 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. “ይሖዋ ጥሩ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት”

(10 ደቂቃ)

ይሖዋ እስራኤላውያንን ከባቢሎን እንደታደጋቸው ሁሉ እኛንም ከሰይጣን ዓለም ታድጎናል (መዝ 107:1, 2፤ ቆላ 1:13, 14)

ለይሖዋ አመስጋኝ መሆናችን በጉባኤ ውስጥ እንድናወድሰው ያነሳሳናል (መዝ 107:31, 32፤ w07 4/15 20 አን. 2)

ይሖዋ ፍቅሩን በገለጸባቸው መንገዶች ላይ ማሰላሰላችን አመስጋኝ ልብ ለማዳበር ይረዳናል (መዝ 107:43፤ w15 1/15 9 አን. 4)

ሥዕሎች፦ ይሖዋን ማወደስ የምንችልባቸው መንገዶች። 1. ወንድሞችና እህቶች በጉባኤ ስብሰባ ላይ ሲዘምሩ። 2. አንድ ወንድም በስብሰባ ላይ ሐሳብ ሲሰጥ። 3. ሁለት እህቶች ከቤት ወደ ቤት ሲያገለግሉ።

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 108:9—ሞዓብ የአምላክ “መታጠቢያ ገንዳ” ተብሎ መጠራቱ ምን ሊያመለክት ይችላል? (it-2 420 አን. 4)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 107:1-28 (th ጥናት 5)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 4)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ስለምንሰጥበት ዝግጅት ለግለሰቡ ንገረው፤ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የአድራሻ ካርድ ስጠው። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 3)

6. ንግግር

(5 ደቂቃ) ijwyp 90—ጭብጥ፦ አሉታዊ አመለካከትን ማስወገድ የምችለው እንዴት ነው? (th ጥናት 14)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 46

7. ይሖዋን በመዝሙር እናመሰግነዋለን

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ይሖዋ በፍርሃት የተዋጡትን እስራኤላውያን ኃያል ከሆነው የግብፅ ሠራዊት በቀይ ባሕር ካዳናቸው በኋላ ሕዝቡ በአመስጋኝነት ስሜት ተገፋፍተው መዝሙር ዘመሩ። (ዘፀ 15:1-19) ይህን አዲስ መዝሙር ግንባር ቀደም ሆነው የዘመሩት ወንዶቹ ናቸው። (ዘፀ 15:21) ኢየሱስና የጥንቶቹ ክርስቲያኖችም ለአምላክ የምስጋና መዝሙር ዘምረዋል። (ማቴ 26:30፤ ቆላ 3:16) እኛም በጉባኤ፣ በወረዳ እና በክልል ስብሰባዎች ላይ በመዘመር ለይሖዋ ያለንን አመስጋኝነት እንገልጻለን። ለምሳሌ አሁን የዘመርነው “ይሖዋ እናመሰግንሃለን” የሚለው መዝሙር ከ1966 አንስቶ በስብሰባዎቻችን ላይ ሲዘመር ቆይቷል።

በአንዳንድ ባሕሎች ውስጥ ወንዶች ሰው ፊት መዘመር ያሳፍራቸው ይሆናል። ሌሎች ደግሞ ድምፃቸው ጥሩ እንዳልሆነ ስለሚሰማቸው ከመዘመር ወደኋላ ይላሉ። ይሁንና በስብሰባዎቻችን ላይ መዘመር የአምልኳችን ክፍል እንደሆነ ማስታወስ ይኖርብናል። የይሖዋ ድርጅት ግሩም ሆነው የተቀናበሩ መዝሙሮችን ለማዘጋጀትና ለእያንዳንዱ ስብሰባ ተስማሚ የሆነ መዝሙር ለመምረጥ ተግቶ ይሠራል። ከዚህ አንጻር ከእኛ የሚጠበቀው ነገር ቀላል ነው፤ የሚጠበቅብን ድምፃችንን አስተባብረን ለሰማዩ አባታችን ያለንን ልባዊ ፍቅርና አድናቆት መግለጽ ብቻ ነው።

ታሪካችን—ከየት ወዴት?—የመዝሙር ስጦታ፣ ክፍል 2 የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

    “ታሪካችን—ከየት ወዴት?—የመዝሙር ስጦታ፣ ክፍል 2” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ሥዕል። ወንድም ፍራንዝ “የመንግሥት አገልግሎት መዝሙር መጽሐፍ” መውጣቱን ሲገልጽ።
  • በ1944 ምን ተከናውኗል?

  • “ታሪካችን—ከየት ወዴት?—የመዝሙር ስጦታ፣ ክፍል 2” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ሥዕል። በሳይቤሪያ የሚኖር አንድ ወንድም፣ የወንድሞችንና እህቶችን መዝሙር ቅጂ ሌሊት ላይ በጃኬቱ ገበር ውስጥ ሲደብቅ።
  • በሳይቤሪያ ያሉ ወንድሞቻችን ለመንግሥቱ መዝሙሮች ያላቸውን አድናቆት የገለጹት እንዴት ነው?

  • “ታሪካችን—ከየት ወዴት?—የመዝሙር ስጦታ፣ ክፍል 2” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ሥዕል። ወንድሞችና እህቶች ትልቅ ስብሰባ ላይ በኦርኬስትራ ታጅበው ሲዘምሩ።
  • የይሖዋ ምሥክሮች ለመዝሙር ትልቅ ቦታ የሚሰጡት ለምንድን ነው?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 18 አን. 6-15

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 73 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ