ከኅዳር 25–ታኅሣሥ 1
መዝሙር 109–112
መዝሙር 14 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. ንጉሡን ኢየሱስን ደግፉ!
(10 ደቂቃ)
ኢየሱስ ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ በይሖዋ ቀኝ ተቀምጧል (መዝ 110:1፤ w06 9/1 13 አን. 6)
በ1914 ኢየሱስ ጠላቶቹን ድል ማድረግ ጀምሯል (መዝ 110:2፤ w00 4/1 18 አን. 3)
የኢየሱስን አገዛዝ ለመደገፍ ራሳችንን በፈቃደኝነት ማቅረብ እንችላለን (መዝ 110:3፤ be 76 አን. 2)
ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ለመንግሥቱ ያለኝን ድጋፍ ለማሳየት የትኞቹን ግቦች ማውጣት እችላለሁ?’
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
መዝ 110:4—በዚህ ጥቅስ ላይ ስለተጠቀሰው ቃል ኪዳን ግለጽ። (w14 10/15 11 አን. 15-17)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) መዝ 109:1-26 (th ጥናት 2)
4. ውይይት መጀመር
(2 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። አንድ ትራክት ተጠቅመህ ውይይት ጀምር። (lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 3)
5. እምነታችንን ማብራራት
(5 ደቂቃ) ሠርቶ ማሳያ። ijwfq 23—ጭብጥ፦ የይሖዋ ምሥክሮች በጦርነት የማይካፈሉት ለምንድን ነው? (lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 4)
6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ
መዝሙር 72
7. መንግሥቱን በታማኝነት መደገፍ የምንችለው እንዴት ነው?
(15 ደቂቃ) ውይይት።
የይሖዋ መንግሥት የጽንፈ ዓለማዊ ሉዓላዊነቱ መገለጫ ነው። (ዳን 2:44, 45) በመሆኑም የአምላክን መንግሥት በትጋት ስንደግፍ የይሖዋን ሉዓላዊነት መደገፋችን ነው።
‘የሰላምን መስፍን’ በታማኝነት ደግፉ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦
የአምላክን መንግሥት በታማኝነት መደገፍ የምንችለው እንዴት ነው?
የአምላክን መንግሥት መደገፍ ከምንችልባቸው ከሚከተሉት መንገዶች ጋር የተያያዘ ጥቅስ ጻፍ።
በሕይወታችን ውስጥ መንግሥቱን ማስቀደም።
ከመንግሥቱ ተገዢዎች የሚጠበቁትን የሥነ ምግባር መሥፈርቶች ማክበር።
ስለ መንግሥቱ ለሌሎች በቅንዓት መናገር።
ለሰብዓዊ መንግሥታት አክብሮት ማሳየት፤ ሆኖም የቄሳር ሕግ ከአምላክ ሕግ ጋር በሚጋጭበት ጊዜ አምላክን መታዘዝ።
8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 18 አን. 16-24