ከነሐሴ 25-31
ምሳሌ 28
መዝሙር 150 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. በክፉ ሰውና በጻድቅ ሰው መካከል ያሉት ልዩነቶች
(10 ደቂቃ)
ክፉ ሰው ፈሪ ነው፤ ጻድቅ ሰው ግን ልበ ሙሉ ነው (ምሳሌ 28:1፤ w93 5/15 26 አን. 2)
ክፉ ሰው በትክክል ማመዛዘን አይችልም፤ ጻድቅ ሰው ግን ጥሩ ውሳኔ ማድረግ ይችላል (ምሳሌ 28:5፤ it-2 1139 አን. 3)
ጻድቅ የሆነ ድሃ ሰው ክፉ ከሆነ ሀብታም ሰው የበለጠ ዋጋ አለው (ምሳሌ 28:6፤ it-1 1211 አን. 4)
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
ምሳሌ 28:14—ይህ ጥቅስ ምን ማስጠንቀቂያ ይዟል? (w01 12/1 11 አን. 3)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) ምሳሌ 28:1-17 (th ጥናት 10)
4. ውይይት መጀመር
(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ጦርነትና ዓመፅ ስለሚጠፋበት ጊዜ ተወያዩ። (lmd ምዕራፍ 5 ነጥብ 5)
5. ውይይት መጀመር
(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ጦርነትና ዓመፅ ስለሚጠፋበት ጊዜ ተወያዩ። (lmd ምዕራፍ 5 ነጥብ 4)
6. ውይይት መጀመር
(2 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። ጦርነትና ዓመፅ ስለሚጠፋበት ጊዜ ተወያዩ። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 4)
7. ውይይት መጀመር
(3 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ጦርነትና ዓመፅ ስለሚጠፋበት ጊዜ ተወያዩ። (lmd ምዕራፍ 2 ነጥብ 4)
መዝሙር 112
8. ዓመፅን ትጠላላችሁ?
(6 ደቂቃ) ውይይት።
የዓመፅ ምንጭ ሰይጣን ዲያብሎስ ነው፤ ኢየሱስ ሰይጣንን “ነፍሰ ገዳይ” በማለት ጠርቶታል። (ዮሐ 8:44) መላእክት ከሰይጣን ጋር ተባብረው ካመፁ በኋላ ደግሞ ዓመፅ ከመስፋፋቱ የተነሳ ምድር በአምላክ ፊት ተበላሽታ ነበር። (ዘፍ 6:11) የሰይጣን ዓመፀኛ ዓለም የሚጠፋበት ጊዜ ሲቃረብ ብዙ ሰዎች ጨካኞችና ራሳቸውን የማይገዙ ሆነዋል።—2ጢሞ 3:1, 3
መዝሙር 11:5ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦
ይሖዋ ዓመፅን ስለሚወዱ ሰዎች ምን ይሰማዋል? ለምንስ?
ተወዳጅ የሆኑ ስፖርታዊ ጨዋታዎችና መዝናኛዎች ዓለም ለዓመፅ ያለውን ፍቅር የሚያሳዩት እንዴት ነው?
ምሳሌ 22:24, 25ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦
የመዝናኛ ምርጫችንና አብረናቸው ጊዜ የምናሳልፋቸው ሰዎች ለዓመፅ ባለን አመለካከት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩት እንዴት ነው?
የመዝናኛ ምርጫችን ዓመፅን እንደምንወድ ሊያሳይ የሚችለው እንዴት ነው?
9. በመስከረም ወር የሚካሄድ ልዩ ዘመቻ
(9 ደቂቃ)
በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ ንግግር። አስፋፊዎች ለዘመቻው ጉጉት እንዲያድርባቸው አድርግ፤ እንዲሁም ጉባኤው ለዘመቻው ያደረገውን ዝግጅት ግለጽ።
“የናፈቀን ሰላም!” (የ2022 የክልል ስብሰባ መዝሙር) የተባለውን ቪዲዮ አጫውት።
10. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) lfb ትምህርት 12-13