የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb25 ሐምሌ ገጽ 12-13
  • ከነሐሴ 18-24

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከነሐሴ 18-24
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2025
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2025
mwb25 ሐምሌ ገጽ 12-13

ከነሐሴ 18-24

ምሳሌ 27

መዝሙር 102 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. እውነተኛ ጓደኞች የሚጠቅሙን እንዴት ነው?

(10 ደቂቃ)

እውነተኛ ጓደኞች የሚያስፈልገንን ምክር በድፍረት ይሰጡናል (ምሳሌ 27:5, 6፤ w19.09 5 አን. 12)

እውነተኛ ጓደኞች ከዘመዶቻችን ይበልጥ ቶሎ ሊደርሱልን ይችላሉ (ምሳሌ 27:10፤ it-2 491 አን. 3)

እውነተኛ ጓደኞች በጎ ተጽዕኖ ያሳድሩብናል (ምሳሌ 27:17፤ w23.09 10 አን. 7)

አንድ ወጣት ወንድም አንድን አረጋዊ ወንድም ከሐኪም ጋር ለመነጋገር ሲረዳው።

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • ምሳሌ 27:21—ውዳሴ የሚፈትነን በምን መንገድ ነው? (w06 9/15 19 አን. 11)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) ምሳሌ 27:1-17 (th ጥናት 5)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ የክርስትና እምነት ተከታይ አይደለም። (lmd ምዕራፍ 6 ነጥብ 5)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። በማስተማሪያ መሣሪያዎቻችን ውስጥ የሚገኝ አንድ ቪዲዮ ተጠቀም። (lmd ምዕራፍ 8 ነጥብ 3)

6. ንግግር

(5 ደቂቃ) ijwyp ርዕስ 75—ጭብጥ፦ ጓደኛዬ ቢበድለኝ ምን ላድርግ? (th ጥናት 14)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 109

7. “ለመከራ ቀን የተወለደ ወንድም”

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ይሖዋ ዓለም አቀፋዊ የወንድማማች ማኅበር ሰጥቶናል፤ በዚያ ውስጥ አፍቃሪ የሆኑ ጓደኞችን ማግኘት እንችላለን። በጉባኤያችን ውስጥ ካሉ በርካታ ወንድሞችና እህቶች ጋር ወዳጃዊ ዝምድና ሊኖረን ቢችልም የቅርብ ወዳጆቻችን የሆኑት ስንቶቹ ናቸው? ጠንካራ ጓደኝነት ለመመሥረት በደንብ መተዋወቅ፣ መተማመን፣ ልብ ለልብ መነጋገር፣ አብሮ ጊዜ ማሳለፍ እንዲሁም እርስ በርስ መረዳዳት ያስፈልጋል። በመሆኑም ጓደኝነት መመሥረትና ይዞ መቀጠል ጊዜና ጥረት ይጠይቃል።

ምሳሌ 17:17ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት ከአሁኑ ከወንድሞቻችን ጋር የቅርብ ጓደኝነት መመሥረታችን ጥበብ የሆነው ለምንድን ነው?

ሁለተኛ ቆሮንቶስ 6:12, 13ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • ይህን ጥቅስ በሥራ ላይ ማዋላችን ጓደኛ ለማግኘት የሚረዳን እንዴት ነው?

“‘ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው’—ወዳጅነት መመሥረት ጊዜ ይወስዳል” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ሥዕል። ኦገስትና ቤን ቤት ውስጥ ባለ የቅርጫት ኳስ መጫወቻ ሜዳ ላይ በሚገኝ ወንበር ላይ ተቀምጠው ኦገስት ለቤን ኳስ ሲሰጠው።

“ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው”—ወዳጅነት መመሥረት ጊዜ ይወስዳል የተባለውን አጭር ድራማ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • ከዚህ አጭር ድራማ ጓደኝነትን በተመለከተ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?

ፈገግ በማለት ወይም ጥሩ ሰላምታ በመስጠት የጓደኝነትን ዘር መዝራት እንችላለን፤ ከዚያም ለግለሰቡ አሳቢነት በማሳየት ውኃ ማጠጣት እንችላለን። አብረን ጊዜ ስናሳልፍ ደግሞ ጓደኝነታችን እያደገ ይሄዳል፤ በመሆኑም ታጋሽ መሆን ይኖርብናል። በውጤቱም ለዘላለም የሚዘልቅ ጓደኝነት ልንመሠርት እንችላለን።

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) lfb ትምህርት 10-11

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 118 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ