የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb25 መስከረም ገጽ 4-5
  • ከመስከረም 15-21

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከመስከረም 15-21
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2025
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2025
mwb25 መስከረም ገጽ 4-5

ከመስከረም 15-21

ምሳሌ 31

መዝሙር 135 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

አንዲት እናትና ልጇ ሶፋ ላይ ተቀምጠው በደስታ ሲያወሩ።

1. አንዲት እናት ከሰጠችው ፍቅራዊ ምክር የምናገኛቸው ትምህርቶች

(10 ደቂቃ)

ይሖዋ ስለ ፆታ ግንኙነትና ስለ ትዳር ያለውን አመለካከት ለልጆቻችሁ አስተምሯቸው (ምሳሌ 31:3, 10፤ w11 2/1 19 አን. 7-8)

ልጆቻችሁ ለአልኮል መጠጥ የይሖዋ ዓይነት አመለካከት እንዲያዳብሩ አስተምሯቸው (ምሳሌ 31:4-6፤ ijwhf ርዕስ 4 አን. 11-13)

ልጆቻችሁ እንደ ይሖዋ ሰዎችን መርዳት እንዲችሉ አስተምሯቸው (ምሳሌ 31:8, 9፤ g17.6 9 አን. 5)

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • ምሳሌ 31:10-31—እስራኤላውያን በዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ያሉ ጥቅሶችን በቃላቸው ለመያዝ ምን ይረዳቸው ነበር? (w92 11/1 11 አን. 7-8)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) ምሳሌ 31:10-31 (th ጥናት 10)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። አንድ ሰው ደግነት የሚንጸባረቅበት ነገር ከተናገረ ወይም ካደረገ በኋላ ውይይት ጀምር። (lmd ምዕራፍ 5 ነጥብ 3)

5. ውይይት መጀመር

(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ሰዎችን ውደዱ በተባለው ብሮሹር ተጨማሪ መረጃ ሀ ላይ ከሚገኙት “ለማስተማር የምንጓጓቸው እውነቶች” መካከል አንዱን አካፍል። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 4)

6. ተመላልሶ መጠየቅ

(5 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 1 2025 የተበረከተለትን ሰው በመጪው ልዩ ንግግር ላይ እንዲገኝ ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 7 ነጥብ 4)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 121

7. ልጆቻችሁ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎችን በጥበብ እንዲጠቀሙ እርዷቸው

(8 ደቂቃ) ውይይት።

አንድ ትንሽ ልጅ በዘመናዊ ስልክ ወይም በታብሌት ላይ የተለያዩ አፕሊኬሽኖችን እየከፈተ ሲጠቀም አይታችሁ ታውቃላችሁ? ብዙውን ጊዜ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎችን መጠቀም ለልጆች ቀላል ነው። የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎችን አጠቃቀም ለመማር በአብዛኛው እርዳታ ባያስፈልጋቸውም እነዚህን መሣሪያዎች በጥበብ መጠቀም የሚችሉበትን መንገድ ለመማር ግን ሁሌም እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ወላጅ ከሆናችሁ፣ ልጆቻችሁ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎችን በጥበብ እንዲጠቀሙ ልታሠለጥኗቸው የምትችሉት እንዴት ነው?

“ጊዜን በአግባቡ መጠቀም” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ሥዕል። ሶፊያ ባሕር ዳርቻ ላይ እየተዝናናች ነው፤ ታብሌቷን እየተጠቀመች ሳለ ውኃ ውስጥ በኳስ እየተጫወተ ያለ ዶልፊን ሳታየው ያመልጣታል።

ጊዜን በአግባቡ መጠቀም የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎችን በመጠቀም በምናሳልፈው ጊዜ ላይ ገደብ ማበጀታችን ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?

  • ጊዜ ልንመድብላቸው የሚገቡ ሌሎች ነገሮች የትኞቹ ናቸው?

ለቤተሰባችሁ መመሪያ በምታወጡበት ወቅት ሌሎች ወላጆች በሚያደርጉት ነገር ከመመራት ይልቅ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ተመሩ። (ገላ 6:5) ለምሳሌ ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁ፦

  • ልጄ የእኔን የኤሌክትሮኒክ መሣሪያ ለመጠቀም አልፎ ተርፎም የራሱን ለመያዝ በሚያበቃ መጠን ራሱን እንደሚገዛና ኃላፊነት እንደሚሰማው አሳይቷል?—1ቆሮ 9:25

  • የልጄን አጠቃቀም ምን ያህል ልከታተል ይገባል?—ምሳሌ 18:1

  • ልጄ የትኞቹን አፕሊኬሽኖችና ድረ ገጾች እንዲጠቀም እፈቅድለታለሁ? የትኞቹንስ እከለክለዋለሁ?—ኤፌ 5:3-5፤ ፊልጵ 4:8, 9

  • ለሌሎች አስደሳችና አስፈላጊ እንቅስቃሴዎች ጊዜ እንዳያጣ በቀን ውስጥ ለምን ያህል ሰዓት እንዲጠቀም ብፈቅድለት ይሻላል?—መክ 3:1

8. ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ

(7 ደቂቃ)

9. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) lfb ትምህርት 18-19

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 2 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ