ከጥቅምት 20-26
መክብብ 9–10
መዝሙር 30 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. ለሚያጋጥሟችሁ ፈተናዎች ተገቢው አመለካከት ይኑራችሁ
(10 ደቂቃ)
ፈተናዎች የይሖዋን ሞገስ እንዳጣን የሚያሳዩ ምልክቶች እንዳልሆኑ እናውቃለን (መክ 9:11፤ w13 8/15 14 አን. 20-21)
በሰይጣን ዓለም ውስጥ ሕይወት ፍትሐዊ እንዲሆን አንጠብቅም (መክ 10:7፤ w19.09 5 አን. 10)
በፈተና ውስጥ ብንሆንም ጊዜ ወስደን ይሖዋ የሰጠንን ስጦታዎች ማጣጣም ይኖርብናል (መክ 9:7, 10፤ w11 10/15 8 አን. 1-2)
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
መክ 9:5—የሞቱ ሰዎች በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? (lff ምዕራፍ 29 ነጥብ 1)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) መክ 10:1-20 (th ጥናት 11)
4. ውይይት መጀመር
(3 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። ካዘነ ሰው ጋር ውይይት ጀምር። (lmd ምዕራፍ 3 ነጥብ 4)
5. ውይይት መጀመር
(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። የኢኮኖሚ ጉዳይ እንደሚያሳስበው ለገለጸ ሰው ሰዎችን ውደዱ በተባለው ብሮሹር ተጨማሪ መረጃ ሀ ላይ ካሉት “ለማስተማር የምንጓጓቸው እውነቶች” መካከል አንዱን አካፍል። (lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 4)
6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ
መዝሙር 47
7. በመከራ ወቅት ሚዛናችንን መጠበቅ
(15 ደቂቃ) ውይይት።
በየዕለቱ ችግሮችና ፈተናዎች ያጋጥሙናል። ይሁንና አንዳንድ ፈተናዎች ድንገተኛና ከባድ ከመሆናቸው የተነሳ በስሜታዊ፣ በአካላዊ አልፎ ተርፎም በመንፈሳዊ እንድንዝል ሊያደርጉን ይችላሉ። ታዲያ በመከራ ወቅት ሚዛናችንን መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው?
ምንም ዓይነት ፈተና ቢያጋጥመን ይሖዋ ምንጊዜም ‘አስተማማኝ መጠጊያችን’ ነው። (መዝ 62:2) በይሖዋ ለመታመን ምክንያታዊ መሆንና ልካችንን ማወቅ ያስፈልገናል። (ምሳሌ 11:2) ድንገተኛ መከራ ሲያጋጥመን ራሳችንን ወይም ቤተሰቦቻችንን ለመንከባከብ፣ ጥበብ የሚንጸባረቅበት ውሳኔ ለማድረግ ወይም የደረሰብንን ሐዘን ለማስተናገድ ጊዜ መውሰድ ሊያስፈልገን ይችላል።—መክ 4:6
በተጨማሪም ይሖዋ እኛን ለማበረታታት አገልጋዮቹን ስለሚጠቀም የሌሎችን እርዳታ ለመቀበል ወይም ለመጠየቅ ፈቃደኛ ልንሆን ይገባል። የእምነት አጋሮቻችሁ ከልብ እንደሚወዷችሁና እናንተን መርዳት እንደሚያስደስታቸው አስታውሱ።
ሁለተኛ ቆሮንቶስ 4:7-9ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦
ከባድ በሚሆንበት ጊዜም እንኳ ዋና ዋናዎቹን መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎቻችንን ለማከናወን የቻልነውን ያህል ጥረት ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው?
ይሖዋ ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦
ይሖዋ ወንድም ሴፕተርንና ባለቤቱን የረዳቸው እንዴት ነው?
የእምነት አጋሮቻቸው የረዷቸው እንዴት ነው?
ከእነሱ ተሞክሮ ሌላስ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) lfb ትምህርት 28፣ የክፍል 6 ማስተዋወቂያ እና ትምህርት 29