ከጥቅምት 13-19
መክብብ 7–8
መዝሙር 39 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. “ወደ ሐዘን ቤት” ሂዱ
(10 ደቂቃ)
ሐዘን የደረሰባቸውን ለማጽናናት ጊዜ መድቡ (መክ 7:2፤ w22.01 16 አን. 9)
የሞተው ግለሰብ የነበሩትን ግሩም ባሕርያት በመጥቀስ አጽናኗቸው (መክ 7:1፤ w19.06 23 አን. 15)
ሐዘን ከደረሰባቸው ሰዎች ጋር አብራችሁ ጸልዩ (w17.07 16 አን. 16)
አስታውሱ፦ ሐዘን የደረሰባቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ ግለሰቡ ከሞተ ከተወሰነ ጊዜ በኋላም የእምነት አጋሮቻቸው ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።—w17.07 16 አን. 17-19
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
መክ 7:20-22—ይህ ጥቅስ ቅር ያሰኘንን ሰው ለማነጋገር ወይም ላለማነጋገር ለመወሰን የሚረዳን እንዴት ነው? (w23.03 31 አን. 18)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
4. ውይይት መጀመር
(2 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። የግለሰቡን ትኩረት የሚስበው ርዕሰ ጉዳይ ምን እንደሆነ ለማወቅ ሞክር፤ ከዚያም ሌላ ጊዜ ለመገናኘት ሁኔታዎችን አመቻች። (lmd ምዕራፍ 2 ነጥብ 4)
5. ውይይት መጀመር
(2 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። (lmd ምዕራፍ 2 ነጥብ 3)
6. ተመላልሶ መጠየቅ
(2 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። jw.org ድረ ገጻችንን ተጠቀም። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 4)
7. እምነታችንን ማብራራት
(5 ደቂቃ) ሠርቶ ማሳያ። ijwfq ርዕስ 50—ጭብጥ፦ የይሖዋ ምሥክሮች የቀብር ሥነ ሥርዓት ምን ይመስላል? (th ጥናት 17)
መዝሙር 151
8. በትንሣኤ ተስፋ ላይ ጠንካራ እምነት አዳብሩ
(15 ደቂቃ) ውይይት።
ካሉን ውድ ንብረቶች አንዱ ይሖዋ የሰጠን የትንሣኤ ተስፋ ነው። ይህ ተስፋ ስለ ይሖዋ ኃይል፣ ጥበብ፣ ምሕረት፣ በተለይ ደግሞ ለእኛ በግለሰብ ደረጃ ስላለው ፍቅር ያስተምረናል።—ዮሐ 3:16
በትንሣኤ ተስፋ ላይ ጠንካራ እምነት ካለን ከሚያጋጥሙን ፈተናዎች አሻግረን ማየት እንችላለን። (2ቆሮ 4:16-18) በተጨማሪም ስደት ሲደርስብን፣ ሕመም ሲያጋጥመን ወይም የምንወደውን ሰው በሞት ስናጣ በተወሰነ መጠን ውስጣዊ ሰላምና መጽናኛ እንድናገኝ ይረዳናል። (1ተሰ 4:13) በትንሣኤ ላይ እምነት ከሌለን እውነተኛ ደስታ ማግኘት አንችልም። (1ቆሮ 15:19) በዚህ ግሩም ተስፋ ላይ ያላችሁን እምነት ለማጠናከር ለምን ግብ አታወጡም?
ዮሐንስ 11:21-24ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦
ማርታ በትንሣኤ ተስፋ ላይ ጠንካራ እምነት እንዳላት ያሳየችው እንዴት ነው?
እምነት በማሳየቷ የተካሰችው እንዴት ነው?—ዮሐ 11:38-44
ጠንካራ እምነት እንዳላቸው ያሳዩ ሴቶችን ምሳሌ ተከተሉ!—ማርታ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦
የትንሣኤ ተስፋን ከፍ አድርጋችሁ የምትመለከቱት ለምንድን ነው?
በትንሣኤ ተስፋ ላይ ያላችሁን እምነት ለማጠናከር ምን ማድረግ ትችላላችሁ?
9. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) lfb ትምህርት 26-27