ከኅዳር 3-9
መኃልየ መኃልይ 1–2
መዝሙር 132 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. እውነተኛ ፍቅር የታየበት ታሪክ
(10 ደቂቃ)
[የመኃልየ መኃልይ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት።]
ሰለሞን ሱላማዊቷን ልጃገረድ አሞግሷቷል፤ እንዲሁም ቁሳዊ ሀብት እንደሚሰጣት ቃል ገብቶላታል (መኃ 1:9-11)
ሱላማዊቷ ልጃገረድ ለእረኛው የነበራት እውነተኛ ፍቅር ለእሱ ታማኝ እንድትሆን ረድቷታል (መኃ 2:16, 17፤ w15 1/15 30 አን. 9-10)
ጠቃሚ ምክር፦ የመኃልየ መኃልይን መጽሐፍ ስታነቡ እየተናገረ ያለው ማን እንደሆነ ለመለየት አዲስ ዓለም ትርጉም ላይ ያለውን “የመጽሐፉ ይዘት” የሚለውን ክፍል ተጠቀሙ።
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
መኃ 2:7—ሱላማዊቷ ልጃገረድ ላላገቡ ክርስቲያኖች ጥሩ ምሳሌ የምትሆነው ለምንድን ነው? (w15 1/15 31 አን. 11)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
4. ውይይት መጀመር
(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ሰዎችን ውደዱ በተባለው ብሮሹር ተጨማሪ መረጃ ሀ ላይ የሚገኝ አንድ እውነት አካፍል። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 3)
5. ተመላልሶ መጠየቅ
(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ሰዎችን ውደዱ በተባለው ብሮሹር ተጨማሪ መረጃ ሀ ላይ የሚገኝ አንድ እውነት አካፍል። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 3)
6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ
(5 ደቂቃ) lff ምዕራፍ 18 ማስተዋወቂያ እና ነጥብ 1-3 (th ጥናት 8)
መዝሙር 46
7. “ለጋስ ሰው ይባረካል”
(15 ደቂቃ) በሽማግሌ የሚቀርብ ውይይት።
ጊዜያችንንና ሀብታችንን በልግስና መስጠታችን በረከት ያስገኛል። በልግስና የሰጠነው ሰው ስጦታችንን እንደ በረከት እንደሚቆጥረው ጥያቄ የለውም። ሆኖም በልግስና የሰጠው ሰውም ይባረካል። (ምሳሌ 22:9) ፈጣሪያችንን በመምሰሉ ደስታ የሚያጣጥም ከመሆኑም በላይ የይሖዋን ሞገስ ያገኛል።—ምሳሌ 19:17፤ ያዕ 1:17
ልግስና ደስታ ያስገኛል የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦
በቪዲዮው ላይ የታዩት ሰዎች ዓለም አቀፉ የወንድማማች ማኅበር ባሳየው ልግስና የተነሳ ደስታ ያገኙት እንዴት ነው?
እነሱስ ለሌሎች በልግስና መስጠት የሚያስገኘውን ደስታ ያጣጣሙት እንዴት ነው?
8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) lfb ትምህርት 32-33