ከኅዳር 10-16
መኃልየ መኃልይ 3–5
መዝሙር 31 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. ውስጣዊ ውበት ያለው ዋጋ
(10 ደቂቃ)
የሱላማዊቷ ልጃገረድ አነጋገር ውስጣዊ ውበቷን ያንጸባርቃል (መኃ 4:3, 11፤ w15 1/15 30 አን. 8)
የሥነ ምግባር ንጽሕናዋ ውብ ከሆነ የአትክልት ቦታ ጋር ተመሳስሏል (መኃ 4:12፤ w00 11/1 11 አን. 17)
ከውጫዊ ውበት ይበልጥ ዋጋ ያለው ውስጣዊ ውበት ማንም ሰው ሊያዳብረው የሚችለው ነገር ነው (g 2/05 9 አን. 2-5)
ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘በሌሎች ላይ ከፍ አድርጌ የምመለከተው የትኞቹን መንፈሳዊ ባሕርያት ነው?’
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
መኃ 3:5—“የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች” “በሜዳ ፍየሎችና በመስክ ላይ ባሉ አጋዘኖች” እንዲምሉ የተደረጉት ለምንድን ነው? (w06 11/15 18 አን. 4)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
4. ውይይት መጀመር
(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀምር በቀጥታ ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 6 ነጥብ 4)
5. ውይይት መጀመር
(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ግለሰቡ jw.org ላይ በራሱ ቋንቋ መረጃ ማግኘት የሚችለው እንዴት እንደሆነ አሳየው። (lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 3)
6. ንግግር
(5 ደቂቃ) ijwbq ርዕስ 131—ጭብጥ፦ መጽሐፍ ቅዱስ መኳኳልንና ጌጣጌጥ ማድረግን በተመለከተ ምን ይላል? (th ጥናት 1)
መዝሙር 36
7. በጌታ ብቻ አግቡ (ዘፍ 28:2)
(8 ደቂቃ)
8. ጥሩ የትዳር ጓደኛ ይወጣችኋል?
(7 ደቂቃ) ውይይት።
የትዳር ጓደኛ እየፈለጋችሁ ነው? ማግባት የሚፈልጉ ሌሎች ክርስቲያኖች እናንተን ሲመለከቷችሁ ግሩም መንፈሳዊ ባሕርያት እንዳሏችሁ አድርገው ይቆጥሯችኋል? አንድ ሰው ለተወሰነ ጊዜ ያህል መንፈሳዊ ሰው መስሎ መቅረብ ቢችልም እንኳ ውሎ አድሮ ውስጣዊ ማንነቱ መጋለጡ አይቀርም።
አንድ መንፈሳዊ ሰው ከሚያሳያቸው ከሚከተሉት ባሕርያት ጋር የሚዛመዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ጻፉ።
ይሖዋን መውደድና በእሱ ማመን
ራስነትን የመጠቀም ወይም ለራስነት የመገዛት ችሎታ
ራስ ወዳድ አለመሆንና የራስን ጥቅም መሥዋዕት የሚያደርግ ፍቅር
ጥሩ የማመዛዘን ችሎታ፣ ሚዛናዊነትና ምክንያታዊነት
ትጋትና ታታሪነት
9. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) lfb ትምህርት 34-35