የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb26 ጥር ገጽ 8-9
  • ከጥር 26–የካቲት 1

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከጥር 26–የካቲት 1
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2026
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2026
mwb26 ጥር ገጽ 8-9

ከጥር 26–የካቲት 1

ኢሳይያስ 28–29

መዝሙር 28 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ይሖዋን በከንፈራችሁ እና በልባችሁ አክብሩ

(10 ደቂቃ)

ኢሳይያስ በዘመኑ የነበሩትን የሃይማኖት መሪዎች ለግብዝነታቸው አውግዟቸዋል (ኢሳ 29:13፤ ip-1 299 አን. 23)

ኢየሱስ፣ ኢሳይያስ የተናገረው ሐሳብ በመጀመሪያው መቶ ዘመን በነበሩት የሃይማኖት መሪዎች ላይ እንደሚሠራ ገልጿል (ማቴ 15:7-9፤ w21.05 9 አን. 7)

ይሖዋ አገልጋዮቹን ‘ከልብ እንዲታዘዙት’ ይጠብቅባቸዋል (ሮም 6:17፤ w24.06 10 አን. 8)

ሥዕሎች፦ 1. አንድ ወንድም ስብሰባ ላይ ክፍል ሲያቀርብ። አጠገቡ ባለው ቴሌቪዥን ላይ በደስታ የቤተሰብ አምልኮ እያደረገ ያለ ቤተሰብ ይታያል። 2. ያው ወንድም ከራሱ ቤተሰብ ጋር አስደሳች የቤተሰብ አምልኮ ሲያደርግ።

የምንሰብከውን ነገር በሥራ ላይ ስናውል ይሖዋ ይመለከታል፤ እንዲሁም ይደሰትብናል

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • ኢሳ 29:1—አርዔል የሚለው ስም ኢየሩሳሌምን ጥሩ አድርጎ የሚገልጻት ለምንድን ነው? (ip-1 296 አን. 19)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) ኢሳ 29:13-24 (th ጥናት 2)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(2 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። የግለሰቡን ትኩረት የሚስበው ርዕሰ ጉዳይ ምን እንደሆነ ለማወቅ ሞክር። ከዚያም ሌላ ጊዜ ለመገናኘት ሁኔታዎችን አመቻች። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 5)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ ባለፈው ውይይታችሁ ወቅት ያነሳውን ጥያቄ መልስ። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 3)

6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

(2 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠና ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 10 ነጥብ 3)

7. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

(4 ደቂቃ) lff ምዕራፍ 18 ነጥብ 6-7 (lmd ምዕራፍ 11 ነጥብ 3)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 89

8. ‘ሁልጊዜ እሱን ደስ የሚያሰኘውን አደርጋለሁ’

(8 ደቂቃ) ውይይት።

በአንድ ወቅት ኢየሱስ ‘ሁልጊዜ ይሖዋን ደስ የሚያሰኘውን አደርጋለሁ’ ብሏል። (ዮሐ 8:29) እኛም እንደ ኢየሱስ ነገሮችን ይሖዋ በሚፈልገው መንገድ ለማከናወን አቅማችን የፈቀደውን ሁሉ እናደርጋለን። እንዲህ ማድረግ ሁልጊዜ ቀላል ወይም አመቺ ባይሆንም ምንጊዜም ጠቃሚ ነው።

ሥዕሎች፦ “ነገሮችን ይሖዋ በሚፈልገው መንገድ ማከናወን” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰዱ ሥዕሎች። 1. ጆኤል አዳምስ። 2. ጋሪክ ዲያዝ። 3. ላርስ ካርልሰን።

ነገሮችን ይሖዋ በሚፈልገው መንገድ ማከናወን የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • እንደ ስደት፣ የሥነ ምግባር ፈተና እና ኩራት ያሉ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን ነገሮችን ይሖዋ በሚፈልገው መንገድ ስለማከናወን ምን ትምህርት አግኝታችኋል?

9. ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ

(7 ደቂቃ)

10. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) lfb ትምህርት 56፣ የክፍል 10 ማስተዋወቂያ እና ትምህርት 57

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 55 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ