ከጥር 19-25
ኢሳይያስ 24–27
መዝሙር 159 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. “አምላካችን ይህ ነው!”
(10 ደቂቃ)
በአምላካችን በይሖዋ የምንኮራበት ብዙ ምክንያት አለን (ኢሳ 25:9፤ cl 15 አን. 21)
በአዲሱ ዓለም በርካታ መልካም ነገሮችን አዘጋጅቶልናል፤ ይህም የተትረፈረፈ ጥሩ ምግብን ያካትታል (ኢሳ 25:6፤ w24.12 6 አን. 14)
የዘላለም ሕይወት ይሰጠናል (ኢሳ 25:7, 8፤ w25.01 28-29 አን. 11-12)
ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘በዚህ ሳምንት የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዬን ሳከናውን ይሖዋ ስለሰጠን ተስፋዎች ለማን መናገር እችላለሁ?’
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
ኢሳ 24:2—ይህ ጥቅስ ተሻሽሎ የወጣው አዲስ ዓለም ትርጉም ያለውን አንድ ገጽታ የሚያሳየው እንዴት ነው? (w15 12/15 17 አን. 1-3)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
4. ውይይት መጀመር
(3 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። የግለሰቡን ትኩረት የሚስበው ርዕሰ ጉዳይ ምን እንደሆነ ለማወቅ ሞክር። jw.org ድረ ገጻችንን ተጠቀም። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 3)
5. ተመላልሶ መጠየቅ
(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ሰዎችን ውደዱ በተባለው ብሮሹር ተጨማሪ መረጃ ሀ ላይ የሚገኝ አንድ እውነት አካፍል። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 4)
6. እምነታችንን ማብራራት
(5 ደቂቃ) ሠርቶ ማሳያ። ijwbq ርዕስ 160—ጭብጥ፦ ኢየሱስ የአምላክ ልጅ ተብሎ የተጠራው ለምንድን ነው? (th ጥናት 3)
መዝሙር 144
7. ለሕክምና ወይም ለቀዶ ጥገና ስትዘጋጁ ሙሉ በሙሉ በይሖዋ ተመኩ
(15 ደቂቃ) ውይይት።
ይሖዋ “ሙሉ በሙሉ [በእሱ] የሚመኩትን” ይጠብቃቸዋል። (ኢሳይያስ 26:3ን አንብብ።) የሕክምና እርዳታ ለሚጠይቁ ሁኔታዎች ስንዘጋጅ ይሖዋ ያደረገልንን ዝግጅቶች በመጠቀም በእሱ ሙሉ በሙሉ እንደምንመካ ማሳየት እንችላለን።
የሕክምና እርዳታ ለሚጠይቁ ሁኔታዎች ተዘጋጅታችኋል? የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦
የሕክምና እርዳታ ለሚጠይቁ ሁኔታዎች ለመዘጋጀት የሚረዱን ሦስት ዝግጅቶች የትኞቹ ናቸው?
የሕክምና መረጃ የሚሰጡ ሰነዶችa የሚጠቅሙን እንዴት ነው?
የሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴን ማነጋገራችን የተሻለ የሚሆነው መቼ ነው?
ስለ እነዚህ ፍቅራዊ ዝግጅቶች ምን ይሰማችኋል?
በኢሳይያስ 26:3 ላይ ይሖዋ “ዘላቂ ሰላም” እንደሚሰጠን ቃል የገባልን መሆኑ የጤና ችግር እንዳይደርስብን እንደሚጠብቀን የሚያመለክት አይደለም። ከዚህ ይልቅ እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲያጋጥመን ድርጅቱ ባደረጋቸው ፍቅራዊ ዝግጅቶች አማካኝነት እንድንረጋጋና ውስጣዊ ሰላም እንድናገኝ ይረዳናል።
8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) lfb ትምህርት 54-55
የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | እና ጸሎት
a ለነፍሰ ጡር እናቶች የተሰጠ መረጃ (S-401)፣ ቀዶ ሕክምና ወይም ኬሞቴራፒ ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች የተሰጠ መረጃ (S-407) እንዲሁም የሕክምና እርዳታ የሚያስፈልገው ልጅ ላላቸው ወላጆች የተዘጋጀ መረጃ (S-55) የተባሉት ሰነዶች ሲያስፈልጓችሁ ሽማግሌዎቻችሁን መጠየቅ ትችላላችሁ።