ከየካቲት 23–መጋቢት 1
ኢሳይያስ 38–40
መዝሙር 4 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
በጥንቷ እስራኤል የነበረ አንድ እረኛ አንዲትን በግ በክንዶቹ አቅፎ
1. “መንጋውን እንደ እረኛ ይንከባከባል”
(10 ደቂቃ)
ይሖዋ ወደ እሱ እንድንቀርብ ለመርዳት ሲል ቃሉን መጽሐፍ ቅዱስን ሰጥቶናል፤ እንዲሁም እስከ ዘመናችን ተጠብቆ እንዲቆይ አድርጓል (ኢሳ 40:8፤ w23.02 2-3 አን. 3-4)
በርኅራኄ ይንከባከበናል (ኢሳ 40:11፤ cl 70 አን. 7)
በግለሰብ ደረጃ ያውቀናል፤ እንዲሁም የሚያጋጥሙንን ችግሮች እንድንቋቋም ይረዳናል (ኢሳ 40:26-29፤ w18.01 8 አን. 4-6)
ለማሰላሰል የሚረዳ ጥያቄ፦ በኢሳይያስ 40:11 ላይ ስለ እረኛ የተሰጠው መግለጫ ስለ ይሖዋ ምን እንዲሰማህ ያደርጋል?
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
ኢሳ 40:3—እነዚህ ቃላት በመጀመሪያው መቶ ዘመን ዓ.ም. ፍጻሜያቸውን ያገኙት እንዴት ነው? (ip-1 400 አን. 7)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) ኢሳ 40:21-31 (th ጥናት 11)
4. ውይይት መጀመር
(2 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። በቅርቡ በስብሰባ ላይ ያገኘኸውን ትምህርት ለግለሰቡ ለመናገር የሚያስችል አጋጣሚ ፍጠር። (lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 3)
5. ውይይት መጀመር
(2 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። መጽሐፍ ቅዱስን ለማስተማር ስለምታከናውነው ሥራ ለግለሰቡ ለመናገር የሚያስችል አጋጣሚ ፍጠር። (lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 4)
6. ተመላልሶ መጠየቅ
(2 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። (lmd ምዕራፍ 7 ነጥብ 5)
7. ደቀ መዛሙርት ማድረግ
(5 ደቂቃ) lff ምዕራፍ 18 ማጠቃለያ፣ ክለሳ እና ግብ። ጥናትህ በይሖዋ ምሥክሮች መካከል ስላለው ፍቅር እንዲገነዘብ ለመርዳት “ምርምር አድርግ” በተባለው ክፍል ውስጥ የሚገኝ አንድ ርዕስ ተጠቀም። (lmd ምዕራፍ 11 ነጥብ 3)
መዝሙር 160
8. ዓመታዊ የአገልግሎት ሪፖርት
(15 ደቂቃ) ውይይት።
ዓመታዊውን የአገልግሎት ሪፖርት በተመለከተ ከቅርንጫፍ ቢሮው የተላከውን ደብዳቤ ካነበብክ በኋላ አድማጮች ከ2025 የይሖዋ ምሥክሮች የአገልግሎት ዓመት ዓለም አቀፍ ሪፖርት ላይ ያገኟቸውን አንዳንድ አበረታች ነጥቦች እንዲናገሩ ጋብዝ። ባለፈው ዓመት ውስጥ የሚያበረታታ ተሞክሮ ላገኙ አስቀድመህ የመረጥካቸው አስፋፊዎች ቃለ መጠይቅ አድርግ።
Based on NASA/Visible Earth imagery
በ2025 የይሖዋ ሕዝቦች ከቤት ወደ ቤት ለማገልገልና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለመምራት ለየት ያለ ትኩረት መስጠታቸውን ቀጥለዋል
ከ2025 የአገልግሎት ዓመት ሪፖርት ላይ የትኞቹን አበረታች ነጥቦች ማካፈል ትፈልጋላችሁ?
9. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) lfb ትምህርት 64-65