ከየካቲት 16-22
ኢሳይያስ 36–37
መዝሙር 150 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. “የተናገሩትን ቃል በመስማትህ አትፍራ”
(10 ደቂቃ)
ራብሻቁ የይሖዋን ሕዝብ ለማስፈራራት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ (ኢሳ 36:1, 2፤ it “ሕዝቅያስ” ቁ. 1 አን. 14-mwbr)
አቅመ ቢስና ረዳት የለሽ እንደሆኑ እንዲሰማቸው ለማድረግ ሞከረ (ኢሳ 36:8፤ ip-1 387 አን. 10)
በይሖዋና አመራር በሚሰጡት ሰዎች በመተማመናቸው አፌዘባቸው (ኢሳ 36:7, 18-20፤ ip-1 388 አን. 13-14)
የይሖዋ ሕዝቦች የሚያስፈራሯቸውን ሰዎች የሚፈሩበት ምክንያት የለም።—ኢሳ 37:6, 7
ለቤተሰብ አምልኮ የሚሆን ሐሳብ፦ “ይሖዋ ሆይ፣ . . . በአንተ እታመናለሁ” የተባለውን ቪዲዮ ከተመለከታችሁ በኋላ ባገኛችሁት ትምህርት ላይ ተወያዩ።
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
ኢሳ 37:29—ይሖዋ በሰናክሬም አፍ ልጓም ያስገባው እንዴት ነው? (it “ልጓም” አን. 4-mwbr)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) ኢሳ 37:14-23 (th ጥናት 2)
4. ውይይት መጀመር
(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ሰዎችን ውደዱ በተባለው ብሮሹር ተጨማሪ መረጃ ሀ ላይ የሚገኝ አንድ እውነት አካፍል። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 4)
5. ውይይት መጀመር
(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። (lmd ምዕራፍ 3 ነጥብ 5)
6. እምነታችንን ማብራራት
(5 ደቂቃ) ሠርቶ ማሳያ። ijwbq ርዕስ 110 አን. 1-4—ጭብጥ፦ ጥምቀት ምንድን ነው? (th ጥናት 17)
መዝሙር 118
7. “ለመሆኑ እንዲህ እንድትተማመን ያደረገህ ምንድን ነው?”
(15 ደቂቃ) ውይይት።
በአምላክ በማመንህ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ በማመንህ ወይም የይሖዋ ምሥክር ለመሆን በመወሰንህ ሰዎች አፊዘውብህ ያውቃሉ? ከሆነ፣ ተጨንቀህ ወይም ፈርተህ ይሆናል። እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ሌሎች የሚናገሩት ነገር ጥርጣሬ እንዲያድርብህ ሊያደርግ ይችላል። ታዲያ ይህ እንዳይሆን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
ኢሳይያስ 36:4ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦
እምነታችን በጠንካራ መሠረት ላይ መገንባቱ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
የወጣትነት ሕይወቴ—በአምላክ ማመን ምክንያታዊ ነው? የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦
ኤሊባልዶ እና ክሪስታል እምነታቸውን ለማጠናከር ምን አድርገዋል?
አምላክ መኖሩን እርግጠኛ እንድትሆን ያደረገህ ምንድን ነው?
በሚከተሉት ነገሮች እንድትተማመን የሚያደርጉህ የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ናቸው?
ይሖዋ እንደሚወድህ
ይሖዋ ምንጊዜም እንደሚረዳህ
እውነተኛዎቹን የአምላክ ሕዝቦች እንዳገኘህ
8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) lfb ትምህርት 62-63