የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 136
  • ማርያም የአምላክ እናት ናት?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማርያም የአምላክ እናት ናት?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • ማርያም ከተወችው ምሳሌ ምን ልንማር እንችላለን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • “እነሆ፣ እኔ የይሖዋ ባሪያ ነኝ!”
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
  • የተሳሳተ ትምህርት 5፦ ማርያም የአምላክ እናት ናት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ማርያም (የኢየሱስ እናት)
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 136
ማርያም ከሕፃኑ ኢየሱስ ጋር

ማርያም የአምላክ እናት ናት?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

አይደለችም። መጽሐፍ ቅዱስ ማርያም የአምላክ እናት እንደሆነች አያስተምርም፤ በተጨማሪም ክርስቲያኖች ማርያምን ሊያመልኳት ወይም እንደ ቅዱስ አድርገው ሊመለከቷት እንደሚገባ አይናገርም።a እስቲ የሚከተለውን አስብ፦

  • ማርያም የአምላክ እናት እንደሆነች ፈጽሞ ተናግራ አታውቅም። መጽሐፍ ቅዱስ ማርያም አምላክን ሳይሆን ‘የአምላክን ልጅ’ እንደወለደች ይናገራል።—ማርቆስ 1:1፤ ሉቃስ 1:32

  • ኢየሱስ ክርስቶስ ማርያም የአምላክ እናት እንደሆነች አንድም ቦታ አልተናገረም፤ የተለየ ክብር ሊሰጣት እንደሚገባም አልጠቀሰም። በአንድ ወቅት አንዲት ሴት፣ ማርያም የእሱ እናት የመሆን አስደሳች መብት በማግኘቷ ምክንያት ለየት ያለ ትኩረት ልትሰጣት ፈልጋ ነበር፤ ኢየሱስ ግን “ደስተኞችስ የአምላክን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው!” በማለት አርሟታል።—ሉቃስ 11:27, 28

  • “የአምላክ እናት” እንዲሁም “ቲኦቶኮስ” (ወላዲተ አምላክ) የሚሉት ሐረጎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኙም።

  • በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ‘የሰማይ ንግሥት’ ተብላ የተጠራችው ማርያም ሳትሆን ከሃዲ የሆኑ እስራኤላውያን ያመልኳት የነበረችው የሐሰት አምላክ ናት። (ኤርምያስ 44:15-19) ‘የሰማይ ንግሥት’ ተብላ የተጠራችው የባቢሎናውያን አምላክ የሆነችው ኢሽታር (አስታርቴ) ሳትሆን አትቀርም።

  • ጥንት የነበሩ ክርስቲያኖች ማርያምን አላመለኩም፤ የተለየ ክብርም አልሰጧትም። አንድ የታሪክ ምሁር እንደገለጹት የጥንቶቹ ክርስቲያኖች “ኑፋቄዎችን ይቃወሙ የነበረ ከመሆኑም ሌላ ለማርያም ተገቢ ያልሆነ ትኩረት መስጠት ‘እንስት አምላክን ያመልካሉ የሚል ጥርጣሬ ያስነሳል’ የሚል ስጋት ሳይፈጥርባቸው አይቀርም።”—ኢን ኩዌስት ኦቭ ዘ ጂዊሽ ሜሪ

  • መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ምንጊዜም እንዳለ ይናገራል። (መዝሙር 90:1, 2፤ ኢሳይያስ 40:28) አምላክ መጀመሪያ ስለሌለው እናት ልትኖረው አትችልም። በተጨማሪም ማርያም አምላክን በማህፀኗ መያዝ አትችልም፤ ምክንያቱም አምላክን ሰማያት እንኳ ሊይዙት እንደማይችሉ መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል።—1 ነገሥት 8:27

ማርያም—የኢየሱስ እንጂ “የአምላክ እናት” አይደለችም

ማርያም አይሁዳዊ ስትሆን የዘር ሐረጓም በንጉሥ ዳዊት በኩል የሚመጣ ነው። (ሉቃስ 3:23-31) ማርያም እምነት ያላትና ለአምላክ ያደረች ሰው ስለነበረች አምላክ በእጅጉ ባርኳታል። (ሉቃስ 1:28) አምላክ የኢየሱስ እናት እንድትሆን መርጧታል። (ሉቃስ 1:31, 35) ማርያምና ባሏ ዮሴፍ ሌሎች ልጆችም ነበሯቸው።—ማርቆስ 6:3

መጽሐፍ ቅዱስ፣ ማርያም የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ሆና እንደነበር ቢናገርም ከዚያ ሌላ ስለ እሷ ተጨማሪ መረጃ አይሰጥም።—የሐዋርያት ሥራ 1:14

አንዳንዶች ማርያም የአምላክ እናት እንደሆነች የሚያምኑት ለምንድን ነው?

ለማርያም የተለየ ክብር መስጠት እንደተጀመረ የሚታሰበው ከአራተኛው መቶ ዘመን መገባደጃ አንስቶ ነው። በወቅቱ በሮም ግዛት ውስጥ የነበረው የመንግሥት ሃይማኖት የካቶሊክ እምነት ነበር። ይህም በርካታ አረማውያን ወደ ክርስትና እንዲለወጡ አደረጋቸው። በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያኗ ቅዱስ ጽሑፋዊ ድጋፍ የሌለውን የሥላሴ ትምህርት ተቀበለች።

የሥላሴ ትምህርት ደግሞ በርካታ የቤተ ክርስቲያኗ ተከታዮች ኢየሱስ አምላክ ከሆነ፣ ማርያም የአምላክ እናት መሆን አለባት ብለው እንዲደመድሙ አደረጋቸው። በ431 ዓ.ም በተደረገው የኤፌሶን ጉባኤ ላይ ቤተ ክርስቲያኗ ማርያም “የአምላክ እናት” ናት በማለት በይፋ አወጀች። ለማርያም አምልኮ አከል ክብር መስጠት የተጀመረውም ከኤፌሶኑ ጉባኤ በኋላ ነው። አረማዊ የነበሩት ሰዎች ቤተ ክርስቲያኗን ሲቀላቀሉ እንደ አርጤምስ (የሮማውያን ዲያና) እና አይስስ የመሳሰሉት እንስት የመራባት አማልክቶቻቸው በድንግል ማርያም ሥዕሎችና ምስሎች ተተኩ።

በ432 ዓ.ም ፖፕ ሲክስተስ ሦስተኛ “ለአምላክ እናት” መታሰቢያ የሚሆን ቤተ ክርስቲያን እንዲገነባ ትእዛዝ አስተላለፉ። ቤተ ክርስቲያኑ የተገነባውም ሮማውያን ልጆች እንዲወለዱ ታደርጋለች ብለው ለሚያመልኳት ለሉሲና ክብር ተገንብቶ በነበረው ቤተ መቅደስ አቅራቢያ ነው። አንዲት ደራሲ ይህን ቤተ ክርስቲያን አስመልክተው ሲናገሩ “አረማውያን ለታላቋ እናት ያቀርቡት የነበረው አምልኮ፣ ሮም ክርስትናን ስትቀበል በማርያም አምልኮ እንደተተካ የሚያሳይ ትልቅ ምሳሌ ነው” ብለዋል።—ሜሪ—ዘ ኮምፕሌት ሪሶርስ

a በርካታ ሃይማኖቶች ማርያም የአምላክ እናት እንደሆነች ያስተምራሉ። ማርያምን “የሰማይ ንግሥት” ወይም ቲኦቶኮስ (በግሪክኛ “ወላዲተ አምላክ” ማለት ነው) ብለው ይጠሯታል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ