የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g97 7/8 ገጽ 22
  • በሴቶች ላይ የሚፈጸም የኃይል ድርጊት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በሴቶች ላይ የሚፈጸም የኃይል ድርጊት
  • ንቁ!—1997
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሴቶች፣ በቤታቸው ውስጥ ይከበራሉን?
    ንቁ!—1995
  • በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት—ዓለም አቀፍ ችግር
    ንቁ!—2008
  • አምላክ የዓመፅ ድርጊቶችን እንዴት ይመለከታል?
    ንቁ!—2002
  • ጠብ ቤተሰብን ሲያናጋ
    ንቁ!—1998
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1997
g97 7/8 ገጽ 22

በሴቶች ላይ የሚፈጸም የኃይል ድርጊት

ናይጄሪያ የሚገኘው የንቁ! መጽሔት ዘጋቢ እንዳጠናቀረው

ሴቶች ገና ከተጸነሱበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ የኃይል ድርጊት ይፈጸምባቸዋል በማለት የተባበሩት መንግሥታት ሂውማን ዴቨሎፕመንት ሪፖርት 1995 (እንግሊዝኛ) ባቀረበው ዘገባ ላይ አትቷል። በዓለም ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶች ከዚህ በታች የሰፈሩት ነገሮች እየተፈጸሙ እንዳሉ አረጋግጧል:-

ከመወለዳቸው በፊት። በአንዳንድ አገሮች በማኅፀን ውስጥ ያለው ሽል ወንድ ወይም ሴት መሆኑን ለይቶ ለማወቅ የሕክምና ምርመራ ይደረጋል። ብዙውን ጊዜም ሴት ሆነው የተገኙት በውርጃ ይቀጠፋሉ።

በልጅነት ጊዜ። በባርባዶስ፣ በካናዳ፣ በኔዘርላንድስ፣ በኒው ዚላንድ፣ በኖርዌይና በዩናይትድ ስቴትስ ከሚኖሩ ከሦስት ሴቶች መካከል አንዷ በልጅነት ወይም በወጣትነት ዕድሜዋ ወቅት በጾታ እንደምትነወር ሪፖርት ተደርጓል። በእስያና በሌሎች ቦታዎችም በየዓመቱ አንድ ሚልዮን የሚሆኑ ልጆች ዝሙት አዳሪ እንዲሆኑ ይገደዳሉ። ከእነዚህም መካከል አብዛኞቹ ልጃገረዶች ናቸው። በዓለም ዙሪያ በሚልዮን የሚቆጠሩ ልጃገረዶች በሚፈጸምባቸው ግርዘት የተነሳ ለሥቃይ ይዳረጋሉ።

በአዋቂነት ዘመን። በቺሊ፣ በሜክሲኮ፣ በፓፑዋ ኒው ጊኒ እና በኮሪያ ሪፑብሊክ ከሚኖሩ ያገቡት ሴቶች መካከል ከሦስቱ ሁለቱ ባሎቻቸው ይደበድቧቸዋል። በካናዳ፣ በኒው ዚላንድ፣ በእንግሊዝና በዩናይትድ ስቴትስ ከሚኖሩ ከስድስት ሴቶች መካከል አንዷ ተገዳ ትደፈራለች።

በቀሪዎቹ የሕይወት ዘመናት። በባንግላዴሽ፣ በብራዚል፣ በኬንያ፣ በፓፑዋ ኒው ጊኒ እና በታይላንድ ሕይወታቸው በሰው እጅ ከጠፋው ሴቶች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የተገደሉት ቀደም ሲል ወይም አሁን አብረዋቸው ይኖሩ በነበሩ የፆታ ጓደኞቻቸው ነው። በአፍሪካ፣ በደቡብ አሜሪካ፣ በአብዛኞቹ የፓስፊክ ደሴቶችና በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ ሴቶች ራሳቸውን እንዲገድሉ የሚያደርጋቸው ዓቢይ ምክንያት በትዳር ጓደኛቸው በሚፈጸምባቸው የኃይል ድርጊት የተነሳ ነው።

በሴቶች ላይ የሚደርሰው የኃይል ድርጊት ብዙ ሰዎች “ተሳዳቢዎች፣” “ርኅራኄ የሌላቸው” እና “ጨካኞች” የሚሆኑበትና መጽሐፍ ቅዱስ ‘የመጨረሻው ቀን’ ብሎ የሚጠራው ዘመን ዓይነተኛ ምልክት ነው። (2 ጢሞቴዎስ 3:1-5፣ ኒው አሜሪካን ባይብል) ይሖዋ አምላክ እነዚህ መከራ የሞላባቸው ‘የመጨረሻ ቀኖች’ ካለፉ በኋላ በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ‘ምንም የሚያስፈራቸው ሳይኖር’ በእርጋታ የሚኖሩበትን ሰላም የሰፈነበት አዲስ ዓለም እንደሚመሠርት ቃል በመግባቱ አመስጋኝ ልንሆን እንችላለን። (ሕዝቅኤል 34:28፤ 2 ጴጥሮስ 3:13) በአምላክ መንግሥት አገዛዝ ሥር ኢየሱስ ክርስቶስ “የሚጮኹትን ድኾች ነፃ ያወጣል፤ ችግረኞችንና የተናቁትን ሰዎች ይታደጋል። ከጭቆናና ከዓመፅ ይታደጋቸዋል።”—መዝሙር 72:12, 14 የ1980 ትርጉም

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ