የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g99 7/8 ገጽ 9-10
  • ማንኛውም አካላዊ ጉድለት የማይኖርበት ጊዜ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማንኛውም አካላዊ ጉድለት የማይኖርበት ጊዜ
  • ንቁ!—1999
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአካል ጉዳተኝነት የሚወገደው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • እግርን ወይም እጅን አጥቶም ደስተኛ ሕይወት መምራት
    ንቁ!—1999
  • የተሻለ ሕይወት እንደሚመጣ ተስፋ ተሰጥቷል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ከባድ እክል ቢኖርብኝም አስደሳች ተስፋ አለኝ
    ንቁ!—2000
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1999
g99 7/8 ገጽ 9-10

ማንኛውም አካላዊ ጉድለት የማይኖርበት ጊዜ

ከአንገቷ በታች ሙሉ በሙሉ ሽባ የሆነች አንዲት ሴት በአንድ ወቅት ስትናገር አብዛኞቹ ሰዎች “ጠንካራና ጤናማ ሰውነት የሚኖራቸው ለተወሰነ ጊዜ” ብቻ ነው ብላለች። ይዋል ይደር እንጂ ሁላችንም በሆነ ወቅት ላይ አካላዊ እክል የሚገጥመን በመሆኑ በእርግጥም ትክክለኛ አባባል ነው! በአሁኑ ጊዜ የመነጽር፣ በዓይን ብሌን ላይ የሚለጠፉ ሌንሶች፣ የሰው ሠራሽ ጥርሶች፣ ለመስማትና የልብን ምት ለማስተካከል የሚያገለግሉ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች እንዲሁም የሰው ሠራሽ እግር ንግድ የደራው በዚህ የተነሳ ነው። ሮሜ 8:22 እንደሚለው “ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ” እየኖረ ነው።

እንግዲያው ሁላችንም አምላክ ጽድቅ በሚሰፍንበት “አዲስ ምድር” ውስጥ ታዛዥ ለሆኑ የሰው ልጆች ፍጹም አካላዊ ጤና እንደሚሰጥ በገባው ቃል ልንጽናና እንችላለን። (2 ጴጥሮስ 3:13፤ ራእይ 21:3, 4) ኢሳይያስ 35:5, 6 “በዚያን ጊዜም የዕውሮች ዓይን ይገለጣል የደንቆሮዎችም ጆሮ ይከፈታል። . . . አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘልላል፣ የድዳም ምላስ ይዘምራል” ይላል።

መጽሐፍ ቅዱስ “እጅግ ብዙ ሰዎች” በዚህ ክፉ ሥርዓት ላይ ከሚደርሰው ጥፋት እንደሚተርፉ አስቀድሞ ተናግሯል። (ራእይ 7:9, 14፤ መዝሙር 37:10, 11, 29) ከዚህ ጥፋት በኋላ ብዙም ሳይቆይ ከባድ አካላዊ ጉድለትና የጤና ችግሮች ያለባቸው ሁሉ ቅጽበታዊ ፈውስ ያገኛሉ! (ኢሳይያስ 33:24) ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት በአምላክ አዲስ ምድር ለሚከናወነው ፈውስ ናሙና ይሆን ዘንድ ተመሳሳይ ፈውስ ፈጽሟል። (ከማርቆስ 5:25-29 እና 7:33-35 ጋር አወዳድር።) በዚያ ወቅት ሰዎች ሰው ሠራሽ እግራቸውን ወይም እጃቸውን፣ ምርኩዛቸውንና ተሽከርካሪ ወንበራቸውን ሲጥሉ የሚኖረውን ልዩ ደስታና የሚፈሰውን የደስታ እንባ መገመት እጅግ ያዳግታል! ጤናማ አካል ስለሚኖራቸው አምላክ የሚሰጣቸውን ምድርን ወደ ገነትነት የመለወጥ ሥራ ለመወጣት ብቁ ይሆናሉ።—ሉቃስ 23:43

እስከዚያው ጊዜ ድረስ ግን በአሁኑ ወቅት ያሉ የአካል ጉዳተኞች ካሉባቸው የአቅም ገደቦች ጋር እየታገሉ መኖር ይኖርባቸዋል። በካናዳ የሚኖር ኔልሰን የተባለ አንድ የአካል ጉዳተኛ “በራሴ ሁኔታ ማዘን ስጀምር በማቴዎስ 24:13 ላይ የሚገኙትን ‘እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል’ የሚሉትን የኢየሱስ ቃላት አስባለሁ” ሲል ተናግሯል። የአካል ጉዳተኞች የአቅም ገደቦች ቢኖሩባቸውም እንኳ በክርስቲያናዊው እምነት በመጽናት ከሁሉ በላቀው መንገድ ማለትም በመንፈሳዊ ምሉአንና ጤናሞች መሆን ይችላሉ።—ያዕቆብ 1:3, 4

የይሖዋ ምሥክሮች በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ይህን እምነት እንዲቀበሉ ረድተዋቸዋል። ከዚህ በፊት ባለው ርዕስ ላይ የተጠቀሰው ዴል የተባለው የአካል ጉዳተኛ “እኔ ያለብኝ ዓይነት አካላዊ ችግሮች ጊዜያዊ መሆናቸውን ባወቅሁ ጊዜ የተሰማኝን ስሜት ለመግለጽ ቃላት ያጥረኛል” ሲል ተናግሯል። አዎን፣ ዴልና እንደ እሱ ያሉ ሌሎች ብዙዎች በእንዲህ ዓይነቱ ተስፋ ስለተበረታቱ አካለ ስንኩላን ሊባሉ አይችሉም።

[በገጽ 10 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ከመጪው ጥፋት የሚተርፉ ሰዎች ከአካላዊ እክሎቻቸው ተአምራዊ በሆነ መንገድ ይፈወሳሉ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ