የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g20 ቁጥር 2 ገጽ 14-15
  • 5. መከራችን የሚያበቃበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 5. መከራችን የሚያበቃበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?
  • ንቁ!—2020
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ይህን ማወቅ ለምን አስፈለገ?
  • ሊታሰብባቸው የሚገቡ ነጥቦች
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • መከራ
    ንቁ!—2015
  • ጥያቄ 3፦ አምላክ መከራ እንዲደርስብኝ የሚፈቅደው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ዓለም አቀፍ ችግር፣ ዓለም አቀፍ መፍትሔ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2020
g20 ቁጥር 2 ገጽ 14-15
አንድ ቤተሰብ ውኃ ዳር ሲዝናና። እርስ በርስ እየተጨዋወቱና እየተሳሳቁ ነው።

5. መከራችን የሚያበቃበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

ይህን ማወቅ ለምን አስፈለገ?

መከራ በእርግጥ የሚያበቃ ከሆነ ይህ ተስፋ ለሕይወታችንም ሆነ ለአምላክ ጥሩ አመለካከት እንዲኖረን ሊያደርግ ይችላል።

ሊታሰብባቸው የሚገቡ ነጥቦች

መከራን ማስወገድ የሚፈልጉ ብዙ ሰዎች አሉ፤ ሆኖም ይህን ለማድረግ የሚያስችል አቅም የላቸውም። እስቲ የሚከተለውን አስብ፦

በሕክምናው ዘርፍ ከፍተኛ እድገት ቢታይም . . .

  • የልብ ሕመም የሰዎችን ሕይወት በመቅጠፍ ረገድ አሁንም የመጀመሪያውን ቦታ እንደያዘ ነው።

  • በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በካንሰር ይሞታሉ።

  • “ዓለማችን ረጅም ጊዜ በቆዩ፣ አዲስ በተፈጠሩና እንደ አዲስ በሚያገረሹ ተላላፊ በሽታዎች አሁንም እየታመሰች ነው” በማለት ዶክተር ዴቪድ ብሉም ፍሮንቲርስ ኢን ኢምዩኖሎጂ በተባለው መጽሔት ላይ ገልጸዋል።

አንዳንድ አገሮች በኢኮኖሚ እየበለጸጉ ቢሆንም . . .

  • በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕፃናት ይሞታሉ፤ ከእነዚህ መካከል አብዛኞቹ የሚኖሩት በድሃ አገሮች ውስጥ ነው።

  • በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች አመቺ የሆነ መጸዳጃ ቤት የላቸውም።

  • በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ንጹሕ የመጠጥ ውኃ አያገኙም።

ሰዎች ስለ ሰብዓዊ መብት ያላቸው ግንዛቤ እየጨመረ ቢመጣም . . .

  • አሁንም ቢሆን በብዙ አገሮች ውስጥ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር በስፋት ይስተዋላል፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያወጣው አንድ ሪፖርት እንደሚያሳየው በርካታ አገሮች “ችግሩ መኖሩን ስላላስተዋሉ ወይም መፍትሔ ለመስጠት የሚያስችል አቅም ስለሌላቸው” ወንጀለኞቹ ለፍርድ ሳይቀርቡ ይቀራሉ።

    ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት

    jw.org ላይ የሚገኘውን የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

አምላክ ያስብልናል።

አምላክ መከራና ሥቃይ ሲደርስብን ያዝናል።

“[አምላክ] የተጨቆነውን ሰው መከራ አልናቀምና፤ ደግሞም አልተጸየፈም፤ ፊቱን ከእሱ አልሰወረም። ለእርዳታ ወደ እሱ በጮኸ ጊዜ ሰምቶታል።”—መዝሙር 22:24

“የሚያስጨንቃችሁንም ነገር ሁሉ በእሱ ላይ ጣሉ፤ ምክንያቱም እሱ ስለ እናንተ ያስባል።”—1 ጴጥሮስ 5:7

መከራ የሚያበቃበት ጊዜ ይመጣል።

መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ዓላማ ሳይፈጸም እንደማይቀር ያረጋግጥልናል።

“አምላክ . . . እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።”—ራእይ 21:3, 4

አምላክ የመከራ መንስኤ የሆኑ ነገሮችን በሙሉ ከሥር መሠረታቸው ያስወግዳል።

አምላክ ይህን የሚያደርገው በመንግሥቱ አማካኝነት ነው።

“የሰማይ አምላክ ፈጽሞ የማይጠፋ መንግሥት ያቋቁማል። ይህም መንግሥት ለሌላ ሕዝብ አይሰጥም። . . . ብቻውን ለዘላለም ይቆማል።”—ዳንኤል 2:44

መከራችን የሚያበቃበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

በሚገባ፤ ሆኖም መከራ የሚወገደው በሰዎች ጥረት አይደለም። መንግሥታት መከራን ለመቀነስ ከመሞከር ባለፈ ምንም ማድረግ አይችሉም፤ አምላክ ግን የመከራ መንስኤ የሆኑ ነገሮችንም ያስወግዳል። ይህን የሚያደርገው በመንግሥቱ አማካኝነት ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ