የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • my ታሪክ 62
  • በዳዊት ቤት ውስጥ ችግር ተፈጠረ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በዳዊት ቤት ውስጥ ችግር ተፈጠረ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ንጉሥ ዳዊት የሠራው ኃጢአት
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • በሕይወታችሁ የሚያጋጥሟችሁን ለውጦች ለመቋቋም በአምላክ መንፈስ ታመኑ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • 2 ሳሙኤል የመጽሐፉ ይዘት
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • መናዘዝ ፈውስ ያስገኛል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
my ታሪክ 62

ምዕራፍ 62

በዳዊት ቤት ውስጥ ችግር ተፈጠረ

ዳዊት በኢየሩሳሌም መግዛት ከጀመረ በኋላ ይሖዋ ሠራዊቱን በጠላቶቻቸው ላይ ብዙ ድል አቀዳጃቸው። ይሖዋ የከነዓንን ምድር ለእስራኤላውያን እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቶ ነበር። ስለዚህ አሁን በይሖዋ እርዳታ ቃል የገባላቸውን ምድር በሙሉ ወረሱ።

ዳዊት ጥሩ ገዥ ነበር። ይሖዋን ይወዳል። በመሆኑም ኢየሩሳሌምን ከያዘ በኋላ በመጀመሪያ ካደረጋቸው ነገሮች መካከል አንዱ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ኢየሩሳሌም ማምጣት ነበር። በተጨማሪም ታቦቱን የሚያስቀምጥበት ቤተ መቅደስ መሥራት ፈለገ።

ዳዊት ትልቅ ሰው ከሆነ በኋላ አንድ ከባድ ስህተት ሠራ። ዳዊት የሌላ ሰው የሆነን ነገር መውሰድ ስህተት እንደሆነ ያውቅ ነበር። ይሁን እንጂ አንድ ቀን ምሽት በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ላይ ሆኖ ወደ ታች ሲመለከት አንድ በጣም ቆንጆ የሆነች ሴት ተመለከተ። ይህች ሴት ቤርሳቤህ ትባላለች፤ ባልዋ ደግሞ ከዳዊት ወታደሮች አንዱ የሆነው ኦርዮ የሚባል ሰው ነው።

ዳዊት ከቤርሳቤህ ጋር የጾታ ግንኙነት የመፈጸም ከፍተኛ ፍላጎት ስላደረበት ወደ ቤተ መንግሥቱ እንድትመጣ አደረገ። ባልዋ በውጊያ ላይ ነበር። ዳዊት ከእሷ ጋር የጾታ ግንኙነት ፈጸመ፤ ከጊዜ በኋላም ቤርሳቤህ እንዳረገዘች አወቀች። ዳዊት በጣም ስለተጨነቀ ኦርዮ እንዲገደል በውጊያው ግንባር ላይ እንዲያሰልፈው ለሠራዊቱ አለቃ ለኢዮአብ መልእክት ላከበት። ኦርዮ ሲገደል ዳዊት ቤርሳቤህን አገባት።

ይሖዋ በዳዊት በጣም ተቆጣ። ስለዚህ የሠራቸውን ኃጢአቶች እንዲነግረው አገልጋዩን ናታንን ላከው። ሥዕሉ ላይ እንደምታየው ናታን ዳዊትን እያነጋገረው ነው። ዳዊት በሠራው ሥራ በጣም አዘነ፤ በመሆኑም ይሖዋ ዳዊትን እንዲሞት አላደረገውም። ይሁን እንጂ ይሖዋ ‘እነዚህን መጥፎ ነገሮች ስለ ሠራህ በቤትህ ውስጥ ብዙ ችግር ይፈጠራል’ አለው። በእርግጥም ዳዊት ብዙ ችግር ገጥሞት ነበር!

በመጀመሪያ የቤርሳቤህ ልጅ ሞተ። ከዚያም የዳዊት የበኩር ልጅ የሆነው አምኖን እህቱ ትዕማር ብቻዋን ከእርሱ ጋር እንድትሆን ካደረገ በኋላ አስገድዷት ከእርሷ ጋር የጾታ ግንኙነት ፈጸመ። የዳዊት ልጅ አቤሴሎም በዚህ ድርጊት በጣም በመናደዱ አምኖንን ገደለው። ከጊዜ በኋላ አቤሴሎም በብዙ ሰዎች ዘንድ ተወዳጅነትን አገኘና ራሱን ንጉሥ አደረገ። በመጨረሻ ከአቤሴሎም ጋር በተደረገው ጦርነት ዳዊት አሸነፈና አቤሴሎም ተገደለ። አዎ፣ ዳዊት ብዙ ችግር አጋጥሞታል።

በዚህ ሁሉ መካከል ቤርሳቤህ ሰሎሞን የሚባል ልጅ ወለደች። ዳዊት ሲያረጅና ሲታመም ልጁ አዶንያስ ራሱን ንጉሥ ለማድረግ ሞከረ። በዚህ ጊዜ ዳዊት ሰሎሞን ንጉሥ እንደሚሆን ለማሳየት ሳዶቅ የተባለ ካህን በራሱ ላይ ዘይት እንዲያፈስበት አደረገ። ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ዳዊት በ70 ዓመት ዕድሜው ሞተ። ዳዊት ለ40 ዓመታት ገዝቷል፤ ከዚያ በኋላ ግን ሰሎሞን የእስራኤል ንጉሥ ሆነ።

2 ሳሙኤል 11:​1-27፤ 12:​1-18፤ 1 ነገሥት 1:​1-48

የአንቀጾቹ ጥያቄዎች

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ