መዝሙር 117
መማር ይኖርብናል
በወረቀት የሚታተመው
1. መንፈስ ይላል፦ “ኑ የሕይወት ውኃ ጠጡ።”
ይሖዋን በማወቅ ተደሰቱ።
አምላክ ጠቃሚ ትምህርት ይሰጣል።
እውነትን ’ሚራብ ሁሉ ይጠግባል።
2. መሰብሰባችንን መቼም ቸል አንበል፤
ከአምላክ መማር ይኖርብናል።
ስብሰባዎቹ ያበረታሉ፤
መንፈሱና ወንድሞች ስላሉ።
3. የውዳሴ መዝሙሮች ያበረታሉ፤
ሥልጡን አንደበት ጣፋጭ ነው ቃሉ።
ካምላክ ሕዝቦች ጋር መሰብሰብ አንተው፤
ሁሌም ’ንገኝ በመካከላቸው።
(በተጨማሪም ዕብ. 10:24, 25ን እና ራእይ 22:17ን ተመልከት።)